Clicky

የሕዝባዊ ስብሰባ ጥሪ

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ሐምሌ 12 ቀን 2006 ዓ.ም. ከቀኑ 7 ሰአት ጀምሮ ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው የመብራት ኃይል አዳራሽ ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሕዝባዊ ስብሰባ ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም በዚህ ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉ ኢዴፓ ደጋፊዎቹን እና የአገር ጉዳይ የሚያሳስባቸውን መላው የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ይጋብዛል፡፡

ኢዴፓ የዛሬውና የወደፊቱ ትውልድ ፓርቲ!!!

ኢዴፓ በመቐለ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው

ኢዴፓ ጠቅላላ ጉባኤውን ሲያካሂድ ባስቀመጠው የሦስተኛ አማራጭነት ሚናውን ወደ ህዝብ የማስረጽ እቅድ አንዱ አካል የሆነው ህዝባዊ ስብሰባ በማካሄድ ከህዝብ ጋር የመወያያ መድረክ ማዘጋጀት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የዚህ አካል የሆነው የአዲስ አበባ ህዝባዊ ስብሰባ እንደተጠናቀቀ ስራ አስፈጻሚው ወደ መቀሌ ጉዞ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡  ስራ አስፈፃሚው የህዝባዊ ስብሰባውን በሌሎች ክልል ከተሞች ላይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከጽ/ቤቱ እንዳገኘነው መረጃ ሌሎች ህዝባዊ ስብሰባው የሚካሄድባቸው የክልል ከተሞች መካከል ባህር ዳር፣ ሃዋሳ፣  ናዝሬት፣ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በ2007 ምርጫ ፓርቲውን ይረዳው ዘንድ በአፋር ክልል አምስቱ ዞኖች በቤንሻንጉል ጉምዝ ስምንት ዞኖችና ወረዳዎች እንዲሁም በአገሪቱም አራቱም አቅጣጫዎች ድርጅታዊ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

የኢዴፓ አመራሮች ስብሰባ እና ስልጠና ላይ ተካፍለው ተመለሱ

የኢዴፓ ስራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫ ቦርድ ከundp ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ስብሰባ እና ስልጠና ላይ ተካፍለው ተመለሱ፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩንና በምርጫ 2007 ፓርቲዎች በሚኖራቸው ተሳትፎ ዙርያ ለማወያየት ለሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ባደረገው ጥሪ መሰረት ኢዴፓን ጨምሮ 8 ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ተካፋይ ሆነዋል፡፡

በቦታው ላይ የተገኙትም የፓርቲ ተወካዮች በጋራና በተናጥል ስለ ፖለቲካ ምህዳሩና ስለ ምርጫ 2007 ተሳትፎአቸው ለundp ተወካዮች አስረድተዋል፡፡ ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት የምርጫ ቦርድ ዋና ጸሃፊ ሲሆኑ በቦታው የተገኙት የፓርቲው የጥናትና ምርምር ሃላፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ የፓርቲውን አቋም ለundp ተወካዮች አስረድተዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ኤርምያስ ባልከው ለ5 ቀናት ደብረ ዘይት በሚገኘው የስራ አመራር ኢንስቲትዩት በግጭት አፈታት (conflict management) ዙርያ በተዘጋጀ ስልጠና ላይ ተካፍለው ተመልሰዋል፡፡ በስልጠናው ላይ ኢህአዴግን ጨምሮ 23 ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ተካፋይ ሆነዋል፡፡  ፓርቲዎቹ በግጭት አፈታት ዙርያ ያላቸውን ተሞከሮ በውይይትና በቡድን ስራ ላይ እርስ በርስ የተለዋወጡ ሲሆን  ችግር እንዳይፈጠርና ችግር ተፈጥሮም ቢገኝ  ፓርቲዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸውና ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህላችን መዳበር እንዳለበት መጠቆማቸውን አክለው ገልጸዋል፡፡

በስልጠናው ማጠቃለያም የምርጫ ቦርድ ዋና ጸሃፊ ለስልጠናው ተካፋዮች የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል፡፡ ይሄ ስልጠና ለ2ኛ ግዜ የተካሄደ ሲሆን በመጀመርያ ዙር በተካሄደው ስልጠና ላይ የፓርቲው የፋይናንስ ሃላፊ አቶ አዳነ ታደሰ ተካፍለው መመለሳቸው የሚታወስ ነው፡፡

ኢዴፓ ለሚቀጥለው አገር አቀፍ ምርጫ ያለውን እንቅስቃሴ ለማጠናከር የሚያስችሉ መዋቅሮችን ፈጠረ

የኢዴፓ የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ በሚቀጥለው አመት ለሚደረገው አገር አቀፍ ምርጫ በአዲስ አበባ እና በሌሎች አካባቢዎች ያለውን እንቅስቃሴ ለማጠናከር  የሚያስችሉ መዋቅሮችን ፈጠረ፡፡ ስለሆነም ዘጠኝ አባላት ያሉት የአዲስ አበባ ጊዜያዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ኃላፊነት በመከፋፈል ሥራ ጀምሯል፡፡

ጊዜያዊ ኮሚቴው ባካሄዳቸው ሁለት ስብሰባዎች አመራሩን መርጧል፡፡ በዚህም መሰረት አቶ ግዛቸው አንመው ሰብሳቢ፣ አቶ መንገሻ ገ/ሚካኤል ም/ሰብሳቢ ፤ አቶ ለማ ጪማ ፀሐፊ፤ ወ/ሪት አለም ዘውዱ ድርጅት ጉዳይ እንዲሁም አቶ አስማማው ተሰማ የኮሚቴው ህዝብ ግንኙነት በመሆን ተመርጠዋል፡፡ በዛሬው እለትም ኮሚቴው ሶስተኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

በተያያዘ ዜናም በቦንጋ፣ በሀዋሳ፣ በወላይታ፣ በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ወሎ እና በሀረርጌ የፓርቲ መዋቅሮች የየአካባቢያቸውን አመራር በመምረጥ የእውቅና ጥያቄ በማቅረብ እውቅና ተሰጥቷቸው ወደስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
[facebook_like_button]

[facebook_send_button]

 

የኢዴፓ ዜና መዋዕል

 

መደበኛውንና የወቅቱን የኢዴፓ ዜና መዋዕል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የኢዴፓ የሥራ አስፈፃሚ የክልል ቢሮዎች ጉብኝት

Ethiopian Democratic Party - visits to Dessie, Lalibela and Dire dawa

የኢዴፓ የሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ወንድወሰን ተሾመና አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ከታህሳስ 25 ቀን  2006 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2006 ዓ.ም ለስድስት ቀናት የቆየ የሥራ ጉብኝት በደሴና በላሊበላ አካሄዱ፡፡ በዚህም ጉብኝት በመጀመሪያ በደሴ አራዳ ገበያ አካባቢ ያለውን ቢሮ የተመለከቱና ቢሮውንም እንዳዲስ ያጠናከረ ሲሆኑ በመቀጠልም በላሊበላ ከተማ ቀደምት በሚባለው ቦታ አካባቢ የሚገኘውን ቢሮ ከተመለከቱና በዛው የሚገኙ አባላትና የኮሚቴ አመራሮችን በፅህፈት ቤትና ከፅህፈት ውጪ በማግኘት ያነጋገሩና የሥራ መመሪያ ያስተላለፉ መሆኑ ታውቋል፡፡

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሴያዊ ፓርቲ (ኢ.ዴ.ፓ) የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ እና የፋይናንስ ኃላፊ የሆኑት አቶ ኤርሚያስ ባልከው እና አቶ አዳነ ታደሰ በሐረር እና በድሬደዋ ከተሞች የፓርቲውን ጽ/ቤት መዋቅር እና የማጠናከር ሥራ ከጥር 27 ቀን 2006 ዓ. ም እስከ ጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም  ሰርተው ተመልሰዋል፡፡

አመራሩ በሐረር ጽ/ቤት ጉዳይና አካባቢው ላይ ያለውን እንቅስቀሴ በምን መልክ ማጠንከር እንደሚችል ከሐረር ኮሚቴ ጋር ገንቢ ውይይት ያደረገ ሲሆን አመራሩ ኮሚቴውን ከላይ ሆኖ ተከታታይ ድጋፍና ክትትል ቢያደርግለት ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ለአመራሩ አረጋግጠዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ከሐረር ጉዞ በኋላ ማለትም በጥር 29 ቀን 2006 ዓ.ም አመራሩ ወደ ድሬደዋ ገብቶ ከድሬደዋ ኮሚቴ ጋር ውይይት ያድረገ ሲሆን፡ የድሬደዋ ኮሚቴ ከሐረር ቢሮ ጋር በመገናኘት በአንድ ላይ ስለሚሰሩበት መንገድ እና በድሬደዋ ከተማ ያለውን እንቅስቃሴ በቀጣይ የሚጠናከርበትን ሁኔታ ላይ ውጤታማ ውይይት አድርጎ በጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ አዲስ አበባ  ተመልሷል፡፡

ኢዴፓ አዲስ ፕሬዚዳንት መረጠ

Chane Kebede, President of Ethiopian Democratic Party

Chane Kebede, President of Ethiopian Democratic Party. Photo – Reporter

የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ማዕከላዊ ምክር ቤት ባለፈው እሑድ ፓርቲውን ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚመሩትን ፕሬዚዳንት መረጠ፡፡

ፓርቲውን በፕሬዚዳንትነት የሚመሩት አቶ ጫኔ ከበደ ናቸው፡፡ከአቶ ጫኔ በተጨማሪ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ዋና ጸሐፊና ዘጠኝ ሥራ አስፈጻሚዎችን መርጧል፡፡ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ባንተይገኝ ታምራት ሲሆኑ፣ ዋና ጸሐፊ ሆነው የተመረጡት አቶ ሳህሉ ባዬ ናቸው፡፡

ቀደም ሲል ፓርቲውን በፕሬዚዳንትነት የመሩት አቶ ሙሼ ሰሙ፣ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሶፊያ ይልማና የፓርቲው ዋና ጸሐፊ አቶ መስፍን መንግሥቱ ሥልጣናቸውን ለአዲሶቹ ተመራጮች አስተላልፈዋል፡፡ አቶ መስፍን ቀደም ሲል በግል ጉዳያቸው ምክንያት ኃላፊነታቸውን በማስረከባቸው ቦታው ባዶ ነበር፡፡

የኢዴፓ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ልደቱ አያሌው ፕሬዚዳንት ለመሆን ዕጩ ሆነው ይቀርባሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ ምክንያቱም ከአንድ ሳምንት በፊት በተካሄደው የኢዴፓ ጠቅላላ ጉባዔ 25 አባላት ያሉት ማዕከላዊ ምክር ቤት አባላትን መምረጡ ይታወሳል፡፡ አቶ ልደቱ የማዕከላዊ ምክር ቤት አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ቀጣዮቹን የፓርቲው ዘጠኝ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንትና ጸሐፊ የሚመርጠው ይህ 25 አባላት ያሉት ማዕከላዊ ምክር ቤት ነው፡፡ አቶ ልደቱ የማዕከላዊ ምክር ቤት አባል ሆነው በመመረጣቸው ፕሬዚዳንት ሆኖ በድጋሚ የመመረጥ አዝማሚያ ታይቷል በሚል የአቶ ልደቱ መመለስ ተጠብቆ ነበር፡፡

ነገር ግን አቶ ሙሼም በድጋሚ ለመመረጥ ፍላጐት ባለማሳየታቸው ኢዴፓ ከዶ/ር አድማሱ ገበየሁ፣ ከአቶ ልደቱ አያሌውና ከአቶ ሙሼ ሰሙ ቀጥሎ አራተኛውን ፕሬዚዳንት ሰይሟል፡፡

አራተኛው ፕሬዚዳንት አቶ ጫኔ ተወልደው ያደጉት በአማራ ክልል ባህር ዳር አካባቢ ነው፡፡ የመጀመርያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እዚያው ተከታትለዋል፡፡

በመቀጠል አስመራ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በሒሳብ ትምህርት የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ሲያገኙ፣ ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በዴቨሎፕመንት ኢኮኖሚክስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አሜሪካ በሚገኘው አትላንቲክ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በርቀት ትምህርት ለማግኘት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡

አቶ ጫኔ በሥራው ዓለም በመምህርነት ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ መሆናቸውና በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው ዲማ ኮሌጅ የተባለ ትምህርት ተቋም ባለቤት ናቸው፡፡ አቶ ጫኔ በፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡

አቶ ጫኔ ኢዴፓ የምሥራቅ ጐጃም ክንፍ እንዲያቋቁም ከማድረግ ጀምሮ እስከ መምራት ድረስ ከመጓዛቸውም በላይ፣ በ1997 ዓ.ም. ቅንጅትን በመወከል ተወዳድረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆነው ነበር፡፡

በአሁኑ ወቅት የፓርቲውን በትረ ሥልጣን ተረክበው የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸውን አንድ ብለው ጀምረዋል፡፡

የዜና ምንጭ – ሪፖርተር

ኢዴፓ በቸሃ ወረዳ እምድብር ከተማ አስራ ሶስተኛ ቢሮውን ከፈተ

የኢትዮጵያውን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኢዴፓ) በቸሃ ወረዳ እምድብር ከተማ  አስራ ሶስተኛ ቢሮውን ቅዳሜ ሕዳር 8 ቀን 2005 ዓ.ም ከፈተ፡፡ የቸሃ ወረዳ የኢዴፓ ደጋፊዎች በተለያየ ጊዜ የፓርቲውን ዓላማዎች፣ አቋሞችና አሰራሮች ላይ ሰፊ ውይይት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን ይህ ውይይታቸው ፍሬያማ  ውጤት ሊያስመዘግብ በመቻሉ፤ የአካባቢው የኢዴፓ ደጋፊ ነዋሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ቢሮ በመክፈት በኢዴፓ እውቅና እንዲሰጣቸው ጥያቄ በማቅረባቸውና ፓርቲው ጥያቄያቸውን በከፍተኛ ውሳኔ በመቀበሉ የቸሃ ወረዳ እምድብር ከተማ ቢሮ ሊከፈት መቻሉ ኢዴፓ አስታወቀ፡፡ [Read more…]

በመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዙሪያ ያለውን ስር የሰደደ ችግር፤ ለችግሩ ምክንያት በሆነ አስተሳሰብና አሰራር መፍታት አይቻልም

በቅርቡ ዜጎች የከተማ ቦታን በሊዝ ብቻ እንዲይዙ የሚያስገድድ አዲስ አዋጅ  ታውጇል፡፡ ይህ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  የታወጀ አዋጅ “ለተሳለጠ፣ ለውጤታማ ለፍትሐዊና ለጤናማ የመሬትና የመሬት ነክ ንብረት ገበያ ልማት፣ ቀጣይነት ለተላበሰ የነጻ ገበያ ሥርዓት መስፋፋት፣ ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲኖር ለማድረግ ”  እንደታወጀ  በዚሁ በአዋጁ ላይ ተጠቅሷል፡፡ [Read more…]

በደቡብ ክልል የደቡብ ምዕራብ ንዑስ ቀጠና ጠቅላላ ጉባኤ

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኢዴፓ)  ባለፈው ዓመት   ባደረገው 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በፓርቲው መተዳደርያ ደንብ መሰረት ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ አመራሩን በአዲስ  መተካቱ ይታወሳል፡፡ [Read more…]