Clicky

“የፕረስ ነጻነት በዴሞክራቲክ ልማታዊ መንግስት ድባብ ውስጥ”

Mushe Semuበሙሼ ሰሙ

“የዴሞክራሲዊ ልማታዊ መንግስትና መገናኛ ብዙሃን ግንኙነት (nexus)” በሚል ርዕስ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባዘጋጀው ሲምፕዚየም ላይ የቀረበ መነሻ ጽሑፍ

ለማንበብ አዚህ ይጫኑ

ስደተኞችን እንደ መንግስት “የገቢ ርዕስ” ከማየት አባዜ ባሻገር

mushe_semu2ከሙሼ ሰሙ

በመጀመርያዎቹ ሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶችን አስመልክቶ ባረቀቀው ደንብ አንቀጽ 18 ላይ ስደተኞችን ወይም መጤዎችን ስለማፈናቀል ድንጋጌ አውጥቶ ነበር፡፡ ድንጋጌው እንደሚያትተው ከሆነ መጠነ ሰፊ በሆነ ደረጃ፣ ያለማመዛዘን፣ ልዩነት ሳያደርግ ሃይል በታከለበት ሁኔታ መጤዎችንና ስደተኞችን ማፈናቀል በሰብአዊ ፍጡር ላይ እንደተሰራ ከባድ ወንጀል ተቆጥሮ አባል ሃገራት በድርጊቱ ፈጻሚ መንግስታት ላይ የጋራ አቋም እንዲወስዱ ስምምነታቸውን የሚጠይቅ ነበር፡፡

ይህ የተባበሩት መንግስታት ደንብ የሁሉንም ሃገራት ይሁንታ በተለያየ ምክንያት ማግኝት ባይችልም፤ በዓለማችን ላይ ስደተኛ የሌለው ሃገር ከቶም ሊገኝ ስለማይችል በመርህ ደረጃ ሁሉም መንግስታት የሚስማሙበት ጉዳይ እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡ የዓለማችን የመጎጎዣ ስርዓት እጅግ በመቀልጠፉና በመዘመኑ፣ የጉዞ ውጣ ውረዳችን ከቀናት ወደ ሰዓታት በመቀነሱ፣ መረጃዎች በስፋትና በጥልቀት በመናኘታቸው ምክንያት ዓለማችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠባለች፡፡ በዚህም ምክንያት የተሻለ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ሕይወት ፍለጋ ቁጥራቸው ይብዛም ይነስ ዜጎቹ ለስደት የማይዳረጉበት ሃገር የለም፡፡ እንግሊዞች ሁለተኛ ሃገራችን ወደሚሏት አሜሪካ ተሰደው፣ ይሰራሉ፡፡ እስራኤሎች፣ የሳኡዲ አረቢያና የአውሮፓ ዜጎች ሳይቀሩ በየሃገሩ በመኖር ሕይወታቸውን ለማቃናት ብሎም ለሃገራቸው ለመትረፍና ከግፍና መከራ ለመሸሽ ይሰደዳሉ፡፡ ዛሬ ላይ ሲወሳ እውነት ሊመስል ባይችልም፤ አብዛኛዎቹ የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ነዋሪዎች ሕይወታቸውን የሚገፉት በስደተኛነት እንደነበረ እጅግ ቢርቅ ከአንድ ትውልድ የማይዘል ሃቅ መሆኑን መረዳት ያሻል፡፡

– ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ –

እውነትም “ያለበት” ይገንበት እንዳይሆን ?

Mushe Semuከሙሼ ሰሙ(የኢዴፓ ፕሬዚዳንት)

“በዓለም ላይ ያሉ  ሃገሮች የራሳቸው መከላከያ ሰራዊት አላቸው፡፡ የኛ መከላከያ ሰራዊት ግን አልጄሪያ የሚባል የራሱ ሃገር አለው፡፡”                                                                         የአልጄሪያ ሕዝብ

አዲስ አድማስ ጋዜጣ በዜና ዘገባው ላይ የመከላከያ ሳምንትን አስመልክቶ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቋማችንን እንድንገልጽ እድል ሰጥቶን ነበር፡፡ በዚህ እድል ሃሳባቸውን ከገለጹት ተጋባዦች መካከል አንዱ እኔ ነኝ፡፡ ዜና ዘጋቢው ለአምዱ ስፋት ይመጥናል ባሉት ልክ ሃሳቤን ቀንጨብ አድርገው በማቅረባቸው በርካታ ሃሳቦቼ በዓምዱ ላይ የመካተት እድል ሊገጥማቸው አልቻለም፡፡ በዚህም ምክንያት በአንባቢያን ዘንድ በቂ ግንዛቤ አልተፈጠረም የሚል ስጋት ነበረኝ፡፡ [Read more…]

Pages: 1 2

አማራጮች ያልቀረቡበት የዘንድሮ ምርጫ!

Mushe Semuከሙሼ ሰሙ

ምርጫዎች ቀን ቆጥረው ይመጣሉ፤ ውጤቱን እንዲለውጡ ግን አንፈልግም”

ሶሻሊስቶች ለህዝብ ጥቅም በሚል ሰበብ በሥልጣን ላይ ለመቆየት የሚሹት በዲሞክራሲያዊ መንገድ አይደለም፡፡ በዚህም ሳቢያ ፍትሃዊ ምርጫ ማድረግ አይዋጥላቸውም፡፡ ተፈጥሯዊ ባህርያቸውም አይደለም፡፡ የእነሱ ዝነኛ ብሂል “የትም ፍጪው [ስልጣኑን] አምጭው” የሚል ነው፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአገራችን በሚካሄዱ ምርጫዎች፣ ምርጫ ቦርድና አስፈጻሚዎቹ ለምርጫ ሕጎችና አሰራሮች አልፎ ተርፎም ለመርሆዎች ተገዢ አለመሆናቸውና ለጉዳዩ ትኩረት መንፈጋቸው ሳያንስ፣ ገዢው ፓርቲ በገሃድ “ተቃዋሚዎች መጡም አልመጡም ግድ የለንም” እስከማለት መድረሱ ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት ፈታኝ ጥያቄ ነው፡፡ የምርጫ ቦርድና የአስፈጻሚዎቹ ትኩረት፣ አማራጭ ሃሳቦች አብብው ሕዝብ በአማራጭ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖረው ማገዝ ሳይሆን እንደ ዓመታዊ በዓል ቀን ቆጥሮ ምርጫውን በማንኛውም ኪሳራ(At any cost) ውስጥ ማስፈፀም እየሆነ የመጣ ይመስላል ፡፡ [Read more…]

ዜጎችን አሳንሶ ራሱን ያገዘፈው “ልማታዊ መንግስት” (ከሙሼ ሰሙ)

Mushe Semu“የምትፈልገውን ሁሉ እሰጥሃለሁ የሚል ግዙፍ መንግስት ያለህን ለመውሰድም ግዙፍ አቅም አለው”

እንደ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ያሉ ግራ ዘመም የቡድን መብት አቀንቃኞች፤የዜጎችን ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ተሳትፎ አሳንሶና ገድቦ ሚናቸውን በመንግስትና በተቋማቱ በመተካት ግዙፍ መንግስትና ጉርድ ዜጋ መፍጠር የፍልስፍናቸው መሰረት ነው፡፡ ምርጫው ነጻና ገለልተኛ ሆነም አልሆነም ወቅቱን የጠበቀ ምርጫ ለሚያካሂዱ አብዮታዊ ዴሞክራቶችና “ልማታዊ መንግስታት”፤በስልጣን ላይ ለግማሽ ምዕተ ዓመት ያህል ለመቆየት ፖለቲካውን መምራትና መቆጣጠር ብቻ በቂ አይደለም፡፡ “ልማታዊ መንግስታት” መንግስታዊ ተቋማትን ተጠቅሞ የኢኮኖሚውና የተፈጥሮ ሃብቱ ማዕከል በመሆን የስራ እድል ፈጣሪ፣ ሃብት አቅራቢ፣የሃብት ፈጠራ ምንጭና መንስኤ ብሎም አከፋፋይና አደላዳይ መሆን ለሕልውናቸው ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ የህዝብ ተሳትፎ ባለበት ከባቢያዊ ሁኔታ ምኞትን ወደ ተግባር ለማሸጋገር የሚያስፈልገው የፈጣሪነትና የአድራጊነት አቅም በቂ ስለማይሆን፤የማይናወጥ፣የማይበረዝና የማይከለስ (ካህሌ ኩሉ) አቅም ለመንግስትና ለተቋማቱ ማቀዳጀት አስፈላጊ ነው፡፡ [Read more…]

ክቡር ሚኒስቴር በመልስዎ ውስጥ ያልነገሩን መልሶች

ላለፉት ስምንት ዓመታት ለመሰረተ ልማት ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት የሰጠው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ልማትንም ሆነ እድገት በማያወላዳ መልኩ ማረጋገጥ አልቻለም፡፡ አወዛጋቢ ቢሆኑም ኢኮኖሚያችን ላለፉት ስምንት ዓመታት ከአምስት ፐርስንት አጠቃላይ ዓመታዊ ምርት እድገት ተነስቶ አሁን ወደ አስር ፐርሰንትና ከዛም በላይ እንዳደገ በርካታ ዋቢዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይህም ሆኖ እድገቱ ያስከተለው ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንደሚወራለት የመሰረተ ልማት፣ የገበያ ትስስርና የምርታማነትን ችግር ፈቶ የኢኮኖሚዊ መዋቅር ሽግግርን  በአስተማማኝ ሁኔታ በማረጋገጥ እድገቱ (Growth) በሂደት ወደ ልማት (Development) ተስፋፍቶ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል የሚችል አስተማማኝ ኢኮኖሚ መሆኑን ማረጋገጥ አለመቻሉ የብዙዎቻችን ጥያቄና የሃገሪቱ ፈተና እንደሆነ መቀጠሉ ግልጽ ነው፡፡ [Read more…]

“የጅብ እርሻ ነገር ሳያድግ በቡቃያው”

ከሙሼ ሰሙ (የኢዴፓ ፕሬዚደንት)
በአንድ ወቅት ወደ ሰሜን ሸዋ ለቅስቀሳ ከተላከው የቅንጅት አመራር ቡድን ጋር ተመድቤ ቅስቀሳውን ካጠናቀቅን በኋላ፣ ከአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር የመወያየት እድል ገጥሞኝ ነበር፡፡ በቅስቀሳው እጅግ ደስተኛ የነበሩት አርሶ አደሮችን ማንን ትመርጣላችሁ ለሚለው ጥያቄ የሰጡኝ መልስ “ቅንጅትን” የሚል ነበር፡፡ [Read more…]

“ሕገ መንግስትና ምርጫ ‘እያነቡ እስክስታ’ ”

ሙሼ ሰሙ

በዚህ ዓመት ሊከናወን በእቅድ የተያዘው የአካባቢና የአዲስ አበባ ምርጫ ሚያዚያ ስድስት ቀን 2005 ዓ.ም እንደሚካሄድ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ አውጥቷል፡፡ ምርጫ ቦርድ እንደተለመደው “ነጻ፣ ሰላማዊ፣ ሚዛናዊና ተአማኒነት” ያለው ምርጫ እንዲሚካሄድ አረጋግጧል፡፡ ምርጫ ቦርድ “ሰላማዊ፣ ነጻ፣ ግልጽና ተአማኒነት” ያለው ሲል ከየትኛው የምርጫ መመዘኛና መስፈርት ተነስቶ እንደሆነ ለመገመት አያዳግትም፡፡ ያው እንደተለመደው በውዝግብ ተጀምሮ በውዝግብ የሚጠናቀቀውን  ዓይነት ምርጫ መሆኑ ነው፡፡ [Read more…]

ለትምህርት ስርዓታችን ህልውና ከፖለቲካዊ ብልጠት ይልቅ ብልህነት ያሻል

በተከበሩ አቶ ሙሼ ሰሙ

ምንጭ አዲስ አድማስ

ትምህርት ዜጎችን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ በመቅረጽ ለራሳቸው፣ ለማህበረሰባቸውና ለሃገራቸው ጠቃሚ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያግዝ የእውቀት ማሸጋገርያ ስልት ነው፡፡ የትምህርት መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ መጣል ከጀመረ ከመቶ ዓመታት በላይ የተቆጠረ ሲሆን ከሁለተኛው አለም ጦርነት በፊት ትምህርት የሚሰጠው በመንግስትና በሃይማኖት ተቋማት ዙርያ ለአስተዳደራዊ ክህሎት፣ ለቀኖናና ለሃይማኖት እውቀት ሲባል እንደነበረ እ.ኤ.አ 2004 ላይ ዮኔስኮ የትምህርት ስርዓትን አስመልክቶ ባዘጋጀው ኮንፍረንስ ላይ የወጡ ዘገባዎች ይገልጻሉ፡፡ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የአፄ ሃይለ ስላሴ ስርዓት ዘመናዊ ትምህርትን በተደራጀ መልኩ በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲሰጡ ሁኔታዎችን ያመቻቸ ቢሆንም የትምህርት ቤቶች እድገት ከማህበረሰቡም ሆነ ከሃይማኖት ተቋማት በገጠመው ተጽእኖ ምክንያት የመስፋፋቱ እድል አዝጋሚ ሆኖ ቆይቷል፡፡ የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል የተደረጉ ተከታታይ ጥረቶችም በወቅቱ ከተከሰተው ኢኮኖሚያዊ ቀውስና ድርቅ ጋር ተዳብለው ለአፄው ስርዓት ውድቀት ምክንያት ሊሆን ችሏል፡፡ [Read more…]

የኢዴፓ ፕሬዚዳንት አቶ ሙሼ ሰሙ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ኢንተርቪው

ዜጎች የከተማ ቦታን በሊዝ ብቻ እንዲይዙ የሚያስገድደውን በቅርቡ የወጣውን አዋጅ በሚመለከት የኢዴፓ ፕሬዚዳንት አቶ ሙሼ ሰሙ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ኢንተርቪው

[Read more…]