Clicky

በሐረር ከተማ የተፈጠረው ችግር አስቸኳይ መፍትሄ ያሻዋል!

ቀን 02/07/2006 ዓ.ም
ቁጥር ኢ.ዴ.ፓ.023/06

የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም ምሽት ሁለት ሰዓት አካባቢ በሐረር ከተማ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ተከስቷል፡፡ ከዚህ በፊትም በዚሁ አካባቢ ተደጋጋሚ የእሳት ቃጠሎዎች መከሰታቸው ይታወሳል፡፡ ችግሩ እንደተከሰተ መንግሥት ድርጊቱን የፈፀመውን አካል ለማወቅ የማጣራትና ህብረተሰቡን የማረጋጋት ሥራ መሥራት ሲገባው በተመሳሳይ ቀን በተቻኮለ ሁኔታ ግሬደር አቅርቦ አካባቢውን ማፅዳት በመጀመሩ ህብረተሰቡ በመንግሥት ላይ የተለያዩ ጥርጣሬዎች እንዲያድሩበት ምክንያት ሆኗል፡፡

በዚህም ምክንያት አላስፈላጊ ግጭት ተፈጥሮ ንብረት ወድሟል፣ የንግድ እንቅስቃሴ ተቋርጧል፣ በሰዎችና በሰላማዊ ህይዎታቸው ላይ መጠኑ ያልተረጋገጠ ጉዳት ደርሷል፡፡ ስለሆነም መንግሥት እንደነዚህ እና መሰል ችግሮች ሲከሰቱ በሰከነ መንገድና ግልፅነት ባለው አሰራር ከህብረተሰቡ ጋር እየተመካከረ መፍታት ይገባዋል ብሎ ኢዴፓ በፅኑ ያምናል፡፡ ህብረተሰቡም ግጭቱ አቅጣጫውን ስቶ ተጨማሪ አላስፈላጊ ጉዳት እንዳይደርስ የበኩሉን አስተዋፅዖ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት የተፈጠረውን ግጭት መንግሥት ቆም ብሎ ችግሩ የተፈጠረበት ምክንያት ምን እንደሆነና ማን እንደፈጠረው በአስቸኳይ አጣርቶ እርምጃ እንዲወስድና በቃጠሎው ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ተገቢውን መፍትሄ በአስቸኳይ እንዲሠጥ ኢዴፓ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

የኢዴፓ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

ሰላምና ህብረ-ብሔራዊነት አላማችን ነው!

ከተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከኢዴፓ የተሰጠ መግለጫ

ከተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የተሰጠ መግለጫ

በፖለቲካም ሆነ በልማት ስም ያለበቂ ዝግጅትና ቅድመ ሁኔታ የተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ኢዴፓ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ባለፉት ዓመታት የአማራው ብሔረሰብ ተወላጆችና ሌሎችም ብሔር-ብሔረሰቦች በብሔረተኝነትና በፖለቲካ ምክንያት ሕይወታቸውን ከመሰረቱበት ቀየ ሲፈናቀሉና ሲሰደዱ መስማት የተለመደ ጉዳይ ነበር፡፡ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የመፈናቀሉ ጉዳይ ጋብ ያለ ቢመስልም የዛሬ ዓመት ገደማ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ከጉራፈርዳ ወረዳ በርካታ የአማራ ተወላጆችን መፈናቀልን ተከትሎ በቅርቡ ከሶማሌ ክልላዊ መንግስት ከጅጅጋ ከተማ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአማራ ተወላጆች መፈናቀላቸው ተዘግቧል፡፡ አሁን በቅርቡ ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት በሺህ የሚቆጠሩ አማራዎች የመፈናቀላቸው ጉዳይ ሰፊ የዜና ሽፋን አግኝቶል ከርሟል፡፡ [Read more…]

ኢህአዴግ በምርጫው ላይ የተቀዋሚውን ሚና ትርጉም አልባ ቢያደርገውም ኢዴፓ በተጽዕኖ ከምርጫ ስርዓቱ ተገፍቶ ባለመውጣት፤ በመርህ ደረጃ ብቻ ለመቆየት ወስኗል !!

ከኢዴፓ የተሰጠ መግለጫ

ምርጫ ዘጠና ሰባት በኢትዮጵያ የምርጫ ፖለቲካ ታሪክ ተጠቃሽ ነው፡፡ ልዩነቶቻቸው እንደተጠበቁ ሆነው ለዚህ ታሪካዊነት እንዲበቃ ያደረጉት ሃይሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የዴሞክራሲ ተቋማት፣ ገዢው ፓርቲ፣ ተቃዋሚዎች ሲሆኑ በተለይ ተጠቃሽ የሚሆነው ደግሞ በተፈጠረው አበረታች ሁኔታ መብቱን ላለማስነጠቅ  በምርጫ ንቁ ተሳትፎ ያደረገው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፡፡ የምርጫው ሒደት የፈጠረው መነቃቃት፣ መከባበር፣ አውቅና መስጠትና ይህ ቀረሽ የማይባል ንቁ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ትንሳኤ እንደነበር ለመዘንጋት አይቻልም፡፡ [Read more…]

በመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዙሪያ ያለውን ስር የሰደደ ችግር፤ ለችግሩ ምክንያት በሆነ አስተሳሰብና አሰራር መፍታት አይቻልም

በቅርቡ ዜጎች የከተማ ቦታን በሊዝ ብቻ እንዲይዙ የሚያስገድድ አዲስ አዋጅ  ታውጇል፡፡ ይህ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  የታወጀ አዋጅ “ለተሳለጠ፣ ለውጤታማ ለፍትሐዊና ለጤናማ የመሬትና የመሬት ነክ ንብረት ገበያ ልማት፣ ቀጣይነት ለተላበሰ የነጻ ገበያ ሥርዓት መስፋፋት፣ ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲኖር ለማድረግ ”  እንደታወጀ  በዚሁ በአዋጁ ላይ ተጠቅሷል፡፡ [Read more…]

ቅድሚ ትኩረት የዜጎችን ህይወት ለማዳን ይሁን

ዛሬም እንደገና የአገራችን ስም በድርቅና በረሃብ ምክንያት የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን መነጋገርያ ርዕስ ሆኖል፡፡ በዝናብ እጥረት ምክንያት በሁሉም የምስራቅ አፍሪካ አገሮች የተከሰተው ድርቅና ረሃቡ  ዓለምን እያነጋገረ ቢሆንም  የድርቅ ውጤት የሆነውን ረሃብ አስቀድሞ ከመተንበይ ጀምሮ ዜጎችን ከሞትና ከስደት ከመከላከል አኳያ የኢህአዴግ መንግስት ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዳልተወጣ ከዓለም አቀፍ ሪፖርቶች መረዳት ይቻላል፡፡ [Read more…]

የ2002 ዓ.ም. አገራዊ ምርጫ ሂደትና ውጤትን አስመልክቶ ከኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የተሰጠ መግለጫ

መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የምርጫ 2002ን ውጤት አስመልክቶ ኢዴፓ ከሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ጋር በተያያዘ የቪኦኤ ዘገባ

[Read more…]

ምርጫ 2002 የሕዝቡ ትክክለኛ ውሳኔ የሚከበርበት፣ ሰላማዊና ፍትሃዊ ምርጫ ሊሆን ይገባል!

ከኢዴፓ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ለሰላማዊ ትግልና ለምርጫ ፖለቲካ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባራዊ ተሳትፎ ሲያሳይ ቆይቷል፡፡ ኢዴፓ የአገራችን የወደፊት ዕጣ-ፈንታ ሊወሰን የሚገባው በሰላማዊ ትግልና በህዝብ ምርጫ ብቻ ነው ብሎ ስለሚያምን ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ በ2002  በሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ ወስኗል፡፡ የወቅቱ የአገራችን የፖለቲካ ምህዳር የቱንም ያህል ችግሮች ያሉበት ቢሆንም እነዚህን ችግሮች ለመፍታትም ሆነ በችግሮቹ ውስጥ አልፎ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚቻለው ራስን ከምርጫ ሂደት በማግለልና አኩራፊ በመሆን ሳይሆን አቅምና ሁኔታ በፈቀደ መጠን ተሳትፎ በማድረግ መሆኑን በማመን ኢዴፓ በመጪው ምርጫ ለመሳተፍ ከመወሰንም አልፎ በምርጫው ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ የሚያስችለውን ዝግጅት ከወዲሁ በተጠናከረ ሁኔታ በመላው አገሪቱ ጀምሯል፡፡

ሙሉዉን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

መድረክ ለዴሞክራሲያዊ ምክክር በኢትዮጵያ የሚባለውን ስብስብ አቋም ይዘን ልንታገለው ወስነናል!

EDP PressRelease Medrek

ከኢዴፓ የተሰጠ መግለጫ

ፓርቲያችን ኢዴፓ ተመስርቶ የአገሪቱን የፖለቲካ መድረክ ከተቀላቀለበት ጊዜ ጀምሮ አብዛኛዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በበጎ አይን ሊያዩት አልዎደዱም፡፡ በአንድ በኩል ፓርቲያችን ኢዴፓ በገዥው ፓርቲ ብቻ ሳይሆን በተቃዋሚው ጎራ ውስጥም የሚታዩ የአመለካከትና የአሰራር ድክመቶችን ጭምር እታገላለሁ በማለት

ሙሉዉን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ከሃዋሳ ከተማ መስተዳድር አዲስ አበባ መስተዳድር ሊማር ይገባዋል!

ከኢዴፓ የተሰጠ መግለጫ

ግንቦት 30 ቀን 2001 ኢዴፓ በሃዋሳ ከተማ ያካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ያለምንም ችግርና መሠናክል በሰላምና በስኬት ተጠናቋል፡፡ ፓርቲው በቅርብ በአዲስ አበባ ከተማ ከአካሄደውም ሆነ ከጥቂት አመታት በፊት በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ሊያካሂዳቸው ከነበሩት ህዝባዊ ስብሰባዎች በተለዬ የሰሞኑ የሃዋሳ ህዝባዊ ስብሰባ በሁለንተናዊ መልኩ ውጤታማ ሆኖ ተጠናቋል፡፡

ሙሉዉን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ