ኢዴፓን መደገፍ ወይም መምረጥ ያልብዎት ምክንያት

፩. ህብረብሄራዊነትና ስላማዊ ትግል ከአንገት በላይ የምናነበንበው ሳይሆን የምር ጽኑ መለያችን ስለሆነ!

፪. ዘመኑን የምንመጥን እውነተኛ የፌዴራሊስት ኃይል ስለሆንን!

፫. በተከታታይ ከሁለት ምርጫ በላይ የፓርቲ ሊቀመንበር መሆን እንደማይቻል በፓርቲያችን ህግ ደንብ አስፍረን፣ ፓርቲውን ከአመራር ግለሰቦች የግል እርስትነት የሚከላከል ብቸኛ ፓርቲ ስለሆነ።

፬. ታሪክ፣ ህግ፣ ፓለቲካ ላይ ተመርኩዙን የኢትዮጵያ የባህር በር ይገባኛል ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ዲፕሎማሲያዊ ትግል ስለምናካሂድ።

፭. ብሄርተኝንት ብቸኛ አማራጭ ሆኖ በሚሰበክበት ዘመን፣ ህብረብሄራዊነት እንደሚቻል በተግባር በማሳየት ፈር የቀደደ ፓርቲ ስለሆንን።

፮. ከተለያዩ ፓርቲዎች ጋር በትብብር እስከ ውህደት በተግባር በመፈጸም፣ የኢትዮጵያን አጀንዳ በጋራ ለማራመድ ምን ያህል ርቀት እንደሚሄድ ያሳየ ብቸኛው ፓርቲ ስለሆነ።

፯. አገራችንን እዚህ ትርምስ ውስጥ ከከተታት ከቡድን መብት ይልቅ ለግለሰብ ነጻነት ቅድሚያ የሚሰጥ ሊብራል ፓለቲካ ስለምናራምድ።