አቶ ልደቱ ከአዲስ አድማስ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

Lidetu Ayalew, Photo (Addis Admas)

Lidetu Ayalew, Photo – Addis Admas

(ምንጭ ፦ አዲስ አድማስ) ከኢዴፓ መስራችና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ልደቱ አያሌው ጋር የተደረገውን ቃለምልልስ ማጠቃለያ በዚህ ሁለተኛ ክፍል እናቀርባለን። የኢትዮጵያ ዋና ዋና ፈተናዎችን ከአረብ አገራት ቀውስ ጋር በማያያዝ፣ እንዲሁም ከአቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት ወዲህ ያለውን የፖለቲካ ሁኔታ ይተነትናሉ። በቅድሚያ ግን በተቃዋሚ ፓርቲዎች ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሁለት በሦስት ጥምረት ውስጥ የመሰባሰብ እድል አላቸው?

ቀጣዩ ምርጫ አንድ አመት ብቻ ነው የቀረው… ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ አንድነት ቢኖር ጥሩ ነበር፡፡ ችግሩ ግን በተቃዋሚ ጐራ ውስጥ የመቻቻል አዝማሚያ የለም፡፡ አንዳንዱ ታቃዋሚ ከሱ የተለየ አመለካከት የምታራምድ ከሆነ አሉባልታ ያስወራል፤ ጥላቻ ያራምዳል፡፡ ይሄ የሚያሳየው ከእኔ አመለካከትና መስመር ውጭ ማራመድ አይቻልም የሚል ስሜታዊ የፅንፍ አስተሳሰብ መያዙን ነው፡፡ በእንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ደግሞ፣ መቻቻልን መፍጠር አይቻልም፡፡ በዚህ ረገድ በ2007 ዓ.ም ምርጫም ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ያመጣል ብዬ አላስብም፡፡

ኢዴፓን በሚመለከት ፓርቲያችን ብቻውን ተዓምር ይፈጥራል የሚል እምነት የለኝም – የፓርላማና የክልል ምርጫ ላይ፡፡ ከፍተኛ ውጤት ሊያመጣ ይችላል ብዬ የማምነው የ‹‹ሶስተኛ አማራጭ››ነት ሚናውን በማጉላት ነው፡፡ ምክንያታዊ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ምትክ የሌለው ምርጫ መሆኑን፤ እንዲሁም ገዢው ፓርቲና አብዛኛው የተቃዋሚ ጐራ እስካሁን የተጓዝንበት መንገድ እንደማይበጀን በማሳየት ረገድ ኢዴፓ ትልቅ ውጤት ያመጣል ብዬ አምናለሁ፡፡ በአግባቡ ከተጠቀምንበት፣ ሃሳባችንን ህብረተሰቡ ጋ ካደረስን፣ አጀንዳችንን በግልጽ ማስረዳት ከቻልን፣ የማይናቅ ውጤት እናመጣለን ብዬ አስባለሁ፡፡ የተወሰኑ መቀመጫዎችን ማሸነፍም እንችላለን፡፡

በእርግጥ የተወሰኑ ወንበሮችን ማግኘት በአገር አቀፍ ደረጃ ያን ያህል ለውጥ ሊያመጣ ይችላል ብዬ አላምንም፡፡ ነገር ግን ዋናው ነገር አመለካከትን ማስተካከል ነው፡፡ ያኔ ዘላቂ ለውጥ ይመጣል፡፡ አብዛኛው ተቃዋሚና ገዢው ፓርቲ አሁን የያዙትን የሁለት ፅንፍ አመለካከት ይዘው እስከቀጠሉ ድረስ ግን፤ ኢዴፓ ውጤት ሊያመጣ የሚችለው በተራዘመ ጊዜ ይሆናል ማለት ነው፡፡

በህብረተሰቡ ውስጥ የኢዴፓን አመለካከት ለማስፋፋት ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልጋል፡፡ ብቻችንን ይሄን ውጤት በአጭር ጊዜ እናመጣለን የሚል አጉል ተስፋ የለኝም፡፡ አሁን አብዛኞቹ ተቃዋሚዎች ኢዴፓ የያዘውን አመለካከትና አቀራረብ ቢቀበሉት ግን፤ ውጤቱ በጣም ፈጣን ይሆናል፡፡

እና ተቃዋሚዎች መሰባሰብ ቢችሉ ውጤት ሊያመጡ ይችላሉ?

መሰባሰብ የሚያስፈልገው፤ ሰላሳ፤ አርባ ፓርቲ ብሎ ለመቁጠር አይደለም፡፡ የሚፈጠረው ስብስብ፣ ከቀድሞዎቹ ስህተቶች በደንብ የተማረ መሆን አለበት፡፡ ያለፉትን ስህተች ላለመድገም የተዘጋጀ መሆን አለበት፡፡ ዝም ብሎ መሰባሰብ ጥቅም የለውም፡፡

“የእስካሁኖቹ ስብስቦች ለምንድን ነው ውጤታማ ያልሆኑት? ህዝቡ የጣለባቸውን ተስፋ እውን ማድረግ ያልቻሉት ለምንድነው?” በእነዚህ ጥያቄዎች ዙሪያ ከታሪክ መማር መቻል አለብን። አሁን ግን ለመማር ብዙም ጥረት አናይም፡፡ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የቀድሞው ቅንጅት ምንም ስህተት ሰርቷል ብለው አያምኑም፡፡ ትክክል ነበር ብለው ያምናሉ፡፡ ካለፈው ስህተት መማር አልቻሉም፡፡ የኢህአዴግ አባል፣ በጭፍን ድጋፍ ሁሉንም ስህተት በተቃዋሚዎች ላይ እንደሚያላክክ ሁሉ፣ እነዚህ ተቃዋሚዎችም በጭፍንነት ሁሉንም ስህተት በኢህአዴግ ላይ ወይም በሌላ አካል ላይ ይለጥፋሉ፡፡

በዚህ መልኩ ለውጥ ሊመጣ አይችልም፡፡ ያለምንም ጥርጥር የተቃዋሚዎች ህብረት አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን፣ የተሻለ ለውጥ ለማምጣት ሲባል እንጂ፣ ህብረት መፍጠር በራሱ ግብ አይደለም። ጥሩ ለውጥ ማምጣት ከፈለግን የቀድሞዎቹ ህብረቶች ለምን ውጤታማ እንዳልሆኑ ቁጭ ብለን ከምር መወያየትና መገምገም አለብን፡፡ ስህተቶችን ቁልጭ አድርገን አውጥተን እነዚህን ስህተቶች፣ “አንደግማቸውም፤ ተምረንባቸዋል” ብለን ልናስተካክላቸው ይገባል፡፡

“መድሎት” በተሰኘው መጽሐፍዎ ላይ፣ የአቶ መለስ አለመኖር የስልጣን ሽኩቻን ያመጣል ብለው ነበር፡፡ አሁንስ የእርሳቸው በህይወት አለመኖር፣ ምን አንደምታዎች ይኖሩታል? ገዢው ፓርቲ ውስጥ ክፍፍል አለ እየተባለ ይወራል፡፡ የርስዎ ስጋት እውን ይሆናል ይላሉ?

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter