ግንቦት 8 ቀን 2001 ኢዴፓ በአዲስ አበባ ከተማ ሕዝባዊ ስብሰባ ያካሂዳል

ኢዴፓ ግንቦት 8 ቀን 2001 ዓ.ም ከቀኑ በ7፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ፣ ሜክሲኮ አደባባይ አጠገብ በሚገኘው የመብራት ኃይል አዳራሽ ሕዝባዊ ስብሰባ ያካሂዳል። ይህ ስብሰባ ኢዴፓ ከግንቦት 1997 ምርጫ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሕዝብ ጋር የሚገናኝበት ስብሰባ ነው።

የስብሰባው ዋነኛ አጀንዳዎች ባለፉት ዓመታት በኢዴፓና በአመራር አባላቱ ላይ ሲናፈሱ በነበሩት አሉባልታዎች ዙሪያ ከሕዝብ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ማጥራት፣ በመጪው ዓመት በሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ምን መደረግ እንዳለበት ከሕዝብ ጋር መመካከር እና በወቅታዊ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየት የሚሉ ናቸው።

ለዚህ ሕዝባዊ ስብሰባ የሚያስፈለገው ዝግጅት በተሟላ ሁኔታ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን፣ ሕዝቡ በስብሰባው ላይ በመገኘት ጥያቄዎቹንና አስተያየቱን ለፓርቲው እንዲያቀርብ ለማድረግ በቀጣይ ቀናት የቅስቀሳ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።
(ከኢዴፓ የውጭ ግንኙነት ዘርፍ)

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter