የኢዴፓ ፕሬዚዳንት ከሁለት አገር አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዚዳንት አቶ ልደቱ አያሌው በአዲስ አበባ ከሚገኙ የሁለት አገሮች አምባሳደሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ከፓርቲው የውጭ ጉዳይ ዘርፍ ያገኘነው መረጃ አመለከተ። አቶ ልደቱ ውይይት ያደረጉት ከኖርዌይ አምባሳደር እና ከጀርመን አምባሳደርና የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ ጋር መሆኑንም የዜና ምንጫችን ጨምሮ ገልጿል።
አቶ ልደቱ ከሁለቱ አገሮች አምባሳደሮች ጋር ያደረጉት ውይይት በተናጠል ሲሆን፤ የውይይቱ አጀንዳዎች ግን ተመሳሳይ ነበሩ ተብሏል። እንደ ዜና ምንጫችን ከሆነ፣ አቶ ልደቱ እና አምባሳደሮቹ “የአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች እና በመጪው ዓመት የሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ” በሚሉ አጀንዳዎች ዙሪያ መወያየታቸው ታውቋል።

የሁለቱ አገሮች አምባሳደሮችና አቶ ልደቱ ሰፋ ያለ ጊዜ ወስደው ያደረጉት ውይይት በመግባባት መንፈስ መካሄዱን የዜና ምንጩ አመልክቶ፣ የኢዴፓና የሁለቱ አገሮች አምባሳደሮች ግንኙነት የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በሁለቱም ወገኖች በኩል ግንዛቤ ተወስዶ መግባባት ላይ ተደርሷል ሲል  ጨምሮ ገልጿል።

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter