ኢዴፓ ለፓርቲዎች በሚሰጠው የፋይናንስ ድጋፍ የማከፋፈያ ደንብ ላይ የማሻሻያ ሃሳብ አቀረበ

መንግስት ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰጠው የፋይናንስ ድጋፍ የሚከፋፈልበት ረቂቅ ደንብ በኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት አማካይነት ተዘጋጅቶ ፓርቲዎች እንዲወያዩበት በቀረበው ጥሪ መሰረት ኢዴፓ የማሻሻያ ሃሳብ ማቅረቡን የፓርቲው ዋና ጸሐፊ አቶ ሙሼ ሰሙ ገለጹ።

የኢዴፓ ተወካይ በውይይቱ ላይ ተገኝተው አስተያየትና ጥያቄ ያቀረቡ መሆናቸውንና፣ ተጨማሪ ማሻሻያዎች ካሉ በጽሑፍ እንዲቀርብ በተገለጸው መሰረት ፓርቲው ያዘጋጀው ማሻሻያ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት የተላከ መሆኑን አቶ ሙሼ አስረድተዋል።

ኢዴፓ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት የላከውን ማሻሻያ ሃሳብ ሙሉ ቃል እዚህ በመጫን ያንብቡ።

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter