ኢህአዴግና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተስማሙባቸው ሰነዶች በርካታ ጉዳዮችን የያዙ መሆናቸው ታወቀ

ኢዴፓ፣ መኢአድ፣ ቅንጅትና ኢህአዴግ ላለፉት ሁለት ወራት ተደራድረው በጋራ ስምምነት የተቀበሏቸው ሁለት ሰነዶች በውስጣቸው በርካታ ጉዳዮችን የያዙ መሆኑ ታወቀ፡፡ እነዚሁ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የሥነ-ምግባር ደንብ” እና “የፖለቲካ ፓርቲዎች የሥነ-ምግባር ደንብን በስራ ላይ ለማዋል የተዘጋጀ መመሪያ” በሚሉ ርዕሶች የተዘጋጁት ሰነዶች በ22 ገፆች የተጠቃለሉ ናቸው፡፡

ከዓለም አቀፍ የዴሞክራሲና የምርጫ ድጋፍ ሰጪ ተቋም (International Institute for Democracy and Electoral Assistance – IDEA) በመባል ከሚታወቀው ተቋም የተወሰደው የፖለቲካ ፓርቲዎች የሥነ-ምግባር ደንብ በዘጠኝ ገፆች የተጠቃለለ ሲሆን፤ ይህንኑ የሥነ-ምግባር ደንብ ለማስፈጸም ይቻል ዘንድ የተለያዩ ሀገሮችን ተሞክሮዎች መሰረት በማድረግ የተዘጋጀው መመሪያ ደግሞ ስምንት አንቀፆችንና በርካታ ንዑሳን አንቀፆችን የያዘ ባለ 13 ገጽ ሰነድ ነው፡፡

የሥነ-ምግባር ደንቡን ለማስፈጸም ይቻል ዘንድ በተዘጋጀው የማስፈጸሚያ መመሪያ በአንቀጽ 6 ላይ በስድስት ክፍሎች (Categories) ተጠቃለው የቀረቡት ወደ 35 የሚጠጉ የጥፋት ዓይነቶች፣ በሀገራችን ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በማገናዘብ የቀረቡ ናቸው ተብሏል፡፡ ለእነዚህም ጥፋቶች ተመጣጣኝ የሆኑ ቅጣቶች በሰነዱ ላይ ተዘርዝረዋል፡፡ ለቅጣቶቹ የሚሰጠውም ውሳኔ ራሳቸው ፓርቲዎቹ በሚያቋቁሙት የጋራ ምክር ቤት፣ በብሔራዊ የምርጫ ቦርድና በፍርድ ቤቶች አማካይነት እንደሆነም በነዚሁ ሰነዶች ላይ ተገልጿል፡፡

ይህንን ደንብ በመፈጸምና በማስፈጸም ረገድ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎች፣ መላው የሀሪቱ ዜጎችና በተለይም የመገኛኛ ብዙሃን ተቋማት ያላቸው ሚናና ኃላፊነት ሳይቀር በሰነዶቹ ውስጥ ተካቷል፡፡ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ሰነዶቹን አያይዘን አቅርበናል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ የስነምግባር ደንብ

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት የፓርቲዎች የምርጫ ስነምግባር ደንብን በስራ ላይ ለማዋል የተዘጋጀ መመሪያ

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter