ተደራዳሪ ፓርቲዎች ዛሬ ተፈራረሙ

የፖለቲካ ፓርቲዎች የስነምግባር ደንብን መፅደቅ በተመለከተ ከተደራዳሪ ፓርቲዎች የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ሥነምግባር ደንብና በደንቡ ማስፈጸሚያ መመሪያ ላይ ባደረጉት ድርድር ስምምነት የተደረሰበት ሰነድ

ኢዴፓ፣ ቅንጅት፣ መኢአድና ኢህአዴግ ላለፉት ሁለት ወራት ተደራድረው የተስማሙበትን ሰነድ በዛሬው ዕለት የተፈራረሙ መሆኑን ከኢዴፓ የውጭ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ አመለከተ፡፡

በሸራተን አዲስ ሆቴል በላሊበላ አዳራሽ በተካሄደው የፊርማ ስነ-ስርዓት ላይ በተደራዳሪ ፓርቲዎቹ የወጣው የጋራ መግለጫ በንባብ ከቀረበ በኋላ፤ የአራቱ ፓርቲዎች ሊቀ መንበሮች ማለትም፤ የኢህአዴግ ሊቀ መንበር አቶ መለስ ዜናዊ፣ የመኢአድ ፕሬዚዳንት ኢንጅኔር ኃይሉ ሻውል፣ የቅንጅት ፕሬዚዳንት አቶ አየለ ጫሚሶ እና የኢዴፓ ፕሬዚዳንት አቶ ልደቱ አያሌው ለፊርማ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ፊርማቸውን በማስቀመጥ በየተራ ንግግር ማድረጋቸው ታውቋል፡፡ (አራቱ ፓርቲዎች የተፈራረሙበት ሰነድና በንባብ የቀረበው የጋራ መግለጫ ከዚህ በታች ቀርቧል)

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter