ፓርቲዎች የተስማሙበት ሰነድ ለፓርላማ ቀረበ

የፖለቲካ ፓርቲዎችን የምርጫ ስነምግባር ለመደንገግ የወጣ ረቂቅ አዋጅ

ክፍል 1

ክፍል 2

ቀደም ሲል አራት ፓርቲዎች በኋላም 65 ፓርቲዎች የተስማሙበት ሰነድ “የፖለቲካ ፓርቲዎችን የምርጫ ስነምግባር ለመደንገግ የወጣ አዋጅ” በሚል ርዕስ በአዋጅ መልክ ተዘጋጅቶ ለፓርላማ መቅረቡ ታወቀ፡፡

በዚሁ ረቂቅ አዋጅ ላይ ሐሙስ ህዳር 24 ቀን 2002 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ውይይት ተደርጐበት ለዝርዝር እይታ ለም/ቤቱ የህግና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ የተመራ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመልክቷል፡፡

በዕለቱ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በተደረገው ስብሰባ የመድረክ አባል ድርጅት የሆነውና በፓርላማ መቀመጫ ያለው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ህብረት የተባለ ፓርቲ “ይህ አጀንዳ መቅረብ የለበትም” የሚል መከራከሪያ አቅርቦ እንደነበር የዜና ምንጩ ጠቁሞ፣ በኢዴፓ በኩል “ህብረት ራሱ በፈጠረው ምክንያት በድርድሩ ስላልተካፈለ አጀንዳውን አይቅረብ ማለቱ ተገቢ አይደለም፡፡ ምርጫው እየተቃረበ ስለሆነ አባሎቻችን በህጉ መንፈስ ተረጋግተው እንዲሰሩ ለማድረግ ይህ አዋጅ በአስቸኳይ መውጣት ይገባዋል” የሚል አስተያየት ተሰጥቷል ሲል አክሎ ገልጿል፡፡

በአዋጁ ላይ ክርክርና ውይይት ከተደረገ በኋላ ቋሚ ኮሚቴው ረቂቅ አዋጁን በዝርዝርና በጥልቀት ተመልክቶ የውሳኔ ሃሳቡን እንዲያቀርብ በአብላጫ ድምፅ ተወስኗል፡፡

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter