ኢዴፓ በፓርላማ ውይይት የሚደረግበት አጀንዳ አቀረበ

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተቀዋሚዎች ቀን ውይይት የሚደረግበት አጀንዳ ያቀረበ መሆኑን በፓርላማ የኢዴፓ ተጠሪ አስታወቁ።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢዴፓ ተጠሪ የሆኑት የተከበሩ አቶ አብዱራህማን አህመዲን በላኩልን መረጃ መሰረት፣ ምክር ቤቱ በተቀዋሚዎች ቀን ውይይት እንዲያደረግበት በኢዴፓ በኩል የቀረበው አጀንዳ “የነዳጅ ዋጋ ተመንና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ የመጣውን የኑሮ ውድነትን” በተመለከተ መሆኑ ታውቋል።
ይህ አጀንዳ ህዳር 1 ቀን 2002 ዓ.ም ለምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ የቀረበ መሆኑን አቶ አብዱራህማን ገልጸው፣ በተመሳሳይ ሁኔታ በአቶ አየለ ጫሚሶ የሚመራው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ሌላ አጀንዳ በማቅረቡ በምክር ቤቱ ደንብ መሰረት በወር አንድ ጊዜ በሚኖረው የተቀዋሚዎች ቀን አንድ አጀንዳ ብቻ እንደሚቀርብ ስለሚደነግግ ከሁለቱ አጀንዳዎች አንዱን ለመምረጥ በምክር ቤቱ መቀመጫ ባላቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአብላጫ ድምጽ የሚወሰን ይሆናል ብለዋል።

በኢዴፓ በኩል የቀረበው አጀንዳው ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል።

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter