“አደይ አበባ” የኢዴፓ የምርጫ ምልክት ሆኖ ተመረጠ

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ቀደም ሲል በተካሄዱ ምርጫዎች ሲጠቀምበት የነበረውን የሁለት ጣቶችን ምስል የያዘ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት እንዲለውጥ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተሰጠው ውሳኔ መሰረት ለውጥ ማድረጉን ከፓርቲው ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመለከተ።

“ከህብረተሰቡ፣ ከፓርቲው አባለትና ደጋፊዎች ደወል፣ ዓይን፣ ሰዓት፣ የቃል ኪዳን ቀለበት፣…” ወዘተ. የሚሉ ከአስር በላይ አማራጮች ተጠቁመው እንደነበር ከጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ አመልክቶ፤ “የአደይ አበባ የአዲስ ዘመን ብሩህ ተስፋ አብሳሪ፣ የከተማውም ሆነ የገጠር ተዋሪዎች በቀላሉ ሊረዱት የሚችሉት በመሆኑና ከፓርቲው ዓላማና በርሖዎች ጋር አብሮ የሚሄድ ሆኖ በመገኘቱ ተመርጧል” ሲል ከጽ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ አስታውቋል።

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter