12 የክርክር አጀንዳዎች ተመረጡ፤ ክርክሩ የካቲት 5 ይጀምራል ተባለ

ግንቦት 15 ቀን 2002 ዓ.ም በሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ በተቃዋሚ ፓርቲዎችና በኢህአዴግ መካከል የሚካሄደው ክርክርና የምረጡኝ ዘመቻ የካቲት 5 ቀን 2002 ዓ.ም እንደሚጀምር ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።
የዜና ምንጩ እንደገለጸው ከሆነ፤ በተቃዋሚ ፓርቲዎችና በኢህአዴግ መካከል ለሚደረገው ክርክር 12 ዋና ዋና አጀንዳዎች መመረጣቸውና እነዚህም አጀንዳዎች በተለያዩ ጊዜአት በሚከናወኑ አስር መድረኮች በሬዲዮና በቴሌቪዥን አማካይነት ለሕዝብ እንደሚቀርቡ ታውቋል።
የካቲት 5 ቀን 2002 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው ክርክር የተመረጠው አጀንዳ “ምርጫና የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” የሚል ርዕስ መሆኑን የዜና ምንጩ ገልጿል። በዚህ የክርክር መድረክ የሚሳተፉት ፓርቲዎች የምርጫ ስነ-ምግባር ደንቡን የፈረሙት ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆኑ መድረክም ጭምር እንደሚሆን የዜና ምንጩ ጨምሮ ገልጿል።

በተቀዋሚ ፓርቲዎች በኩል ይህ ክርክር በሬዲዮና በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭ እንዲተላለፍ ቢጠይቁም፤ በኢህአዴግ በኩል “ክርክሩ የመጀመሪያ በመሆኑ ተቀርፆ መሰራጨት አለበት” የሚል ሃሳብ ቀርቦ በዚሁ ተስማምተዋል ሲል የዜና ምንጩ አስታውቋል።

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter