የምርጫ ቅስቀሳ ከተጀመረ ወዲህ የኢዴፓ ተቀባይነት ጨምሯል ተባለ

ከምርጫ 97 በኋላ ከቅንጅት ተለይቶ በወሰደው አቋም ምክንያት ለዓመታት የዘለቀ አሉባል ሲነዛበት የከረመው የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፤ በሕዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለና ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገረ መምጣቱን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ።
“ኢዴፓ፤ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ያቀረባቸውን የቅስቀሳ ዝግጅቶች ለየት ባለ አቀራረብ በማቅረቡ የአድማጭንና የተመልካችን ቀልብ ለመሳብ ችሏል” ሲል የዜና ምንጩ ጠቅሶ፤ በተለይም በሁለቱ መድረኮች በተደረገው ክርክር ኢዴፓ ከገዢው ፓርቲ ጋር ያለውን ልዩነት ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ተቃዋሚዎች ጋር ያለውን የሃሳብ የበላይነት ማረጋገጥ ችሏል” በማለት ጨምሮ ገልጿል።

ይህም የሃሳብ የበላይነት በርካታ አባላትና ደጋፊዎችን ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት እንዲጎርፉ እያደረገ ሲሆን፣ በስልክና በኢሜይል ጭምር በርካታ የድጋፍ መልእክቶች ለፓርቲው ጽ/ቤት እየደረሱ መሆኑም ታውቋል።

በአጠቃላይ፤ ኢዴፓ ሰሞኑን ባካናወናቸው የቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ስራዎቹ መነሻነት በህብረተሰቡ ዘንድ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ መሰንበቱን የዜና ምንጩ ገልጿል።

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter