የኢዴፓ የምርጫ ማንፌስቶ ታተመ

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ ያደረገው የ2002 ዓ.ም የምርጫ ማንፌስቶ በመጽሕፍ መልክ በማተሚያ ቤት መታተሙን ከፓርቲው ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመለከተ።
የፓርቲው ጽሕፈት በላከልን መረጃ መሰረት ማንፌስቶው በአስር ሺህ ቅጂዎች መታተሙ ታውቋል። የፓርቲው እጩ ተወደዳሪዎች እና አባላቱ ወደ ሕዝቡ ቀርበው የምረጡኝ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት የዚህን ሰነድ ፍሬ ሃሳቦች እንደሚያብራሩ የዜና ምንጩ ጠቅሶ፣ ይህም ሕዝቡ የፓርቲውን ዓላማ በአግባቡ ተገንዝቦ ለመምረጥ ያስችለዋል ብሏል።

ይኸው በሰላሳ ሁለት ገፆች የተካተተው የኢዴፓ የምርጫ 2002 ማንፍስቶ፣ በአዘገጃጀቱም ሆነ በይዘቱ ከሌሎች ፓርቲዎች የተለየ አቀራረብ ያለውና የፓርቲውን አማራጭ ፖሊሲዎች የሚያሳይ መሆኑ ይስተዋላል።

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter