የአውሮፓ ህብረት የታዛቢ ቡድን በቅድሚያ የኢዴፓን አመራር አነጋገረ

በአገራችን ግንቦት 15 ቀን 2002 ዓ.ም የሚካሄደውን አገር አቀፍ ምርጫ ለመታዘብ የመጣው የአውሮፓ ህብረት የታዛቢ ቡድን የኢዴፓን አመራር ማነጋገሩን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ።
የአውሮፓን ህብረት የታዛቢ ቡድን የሚመሩት ሚስተር ቲ-በርማን እና ሌሎች የቡድኑ አባላት ከኢዴፓ አመራር ጋር የተገናኙት ዓርብ ዕለት ከሰዓት በኋላ መሆኑ ታውቋል። የልዑካን ቡድኑ መሪ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ተራ በተራ እንደሚያነጋግሩ ጠቅሰው፣ ይህንኑ ተግባር በኢዴፓ መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

የታዛቢ ቡድኑ የምርጫውን ሂደት፣ ዴሞክራሲያዊነትና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን እንደሚከታተልና በሚያደርገውም እንቅስቃሴ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት በማድረግ ስራውን እንደሚያከናውን አስታውቋል።

በኢዴፓም በኩል ምርጫው ነፃ፣ ፍትሀዊና በመራጩ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ጠቅሶ፤ እስከ አሁን በተደረገው እንቅስቃሴ አልፎ አልፎ መለስተኛ ችግሮች ያጋጠሙ መሆኑንና እነዚህንም ችግሮች በተፈጠረው የፓርቲዎች ምክር ቤት በኩል እየተመካከሩ ለመፍታት ጥረት መደረጉን አስታውቋል።

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter