ኢዴፓ ዓርብ እለት በመቀሌ ስብሰባ ያካሂዳል

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ዓርብ ግንቦት 6 ቀን 2002 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ ሕዝባዊ ስብሰባ እንደሚያካሂድ ከፓርቲው ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመለከተ።
የምረጡኝ ቅስቀሳ የሚደረግበት ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት ሕዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ በእቅድ ከያዛቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ መቀሌ መሆኑን ጽ/ቤቱ ጠቅሶ፣ ስብሰባውን የተሳካ ለማድረግ በስፍራው የሚገኙ አባላት ቅድመ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ መሆናቸውን ጨምሮ ገልጿል።

በዚሁ መሰረት፣ ስብሰባው የሚካሄድበትን ቀን በመግለጽ አዳራሽ ለማግኘት ለክልሉ የመንግስት አካላት ደብዳቤ የተጻፈ መሆኑን ጽ/ቤቱ ገልፆ፤ ይህንኑ ስራ ለማስተባበርና የቅስቀሳ ስራውን ለማከናወን በአቶ ነፃነት ደመላሽ የተመራ ቡድን ወደ ስፍራው መንቀሳቀሱን አመልክቷል።

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter