የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ አካሂደ፡፡

Leaders of Ethiopian Democratic Party

Leaders of Ethiopian Democratic Party

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ቅዳሜ መጋቢት 11 ቀን 2003 ዓመተ ምህረት በተሳካ ሁኔታ አካሂደ፡፡ በመቀጠልም መጋቢት 12 ቀን 2003 ዓመተ ምህረት የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮችና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን የመረጠ ሲሆን የዘርፍ ድልድልም አድረጓል፡፡

በዚሁ ድርጅታዊ ስብሳባ ላይ ፓርቲው ከአባላት ጋር 11 ሳምነታትን የፈጀ ውይይት በማድረግ  10 ነጥብ ያሉት  ሰነድ በረቂቅነት ለጉባኤው ያቀረበ ሲሆን  ጉባኤው ተጨማሪ ውይይት አድርጎ በማዳበር የፓርቲውን 5ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ  ሰነድ አድርጎ አጽድቆታል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በኦዲትና ኢኒስፔክሽን የቀረበውን የፓርቲውን የኦዲት ሪፖርት አድምጦ ከተወያየበት በኋላ የጠቅላላው ጉባኤ ሰነድ አካል እንዲሆን ወስኖል፡፡

በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ዓበይት ከነበሩት ክንውኖች መካካል የፓርቲውን ከፍተኛ የስልጣን አካል የሆነውን የማዕከላዊ ምክር ቤቱን አባላት መምረጥ ሲሆን ይህንኑ ምርጫም ለማስፈጸም ከመካከሉ 3 አስመራጭ አካላትን በመምረጥ ምርጫውን አከናውኗል፡፡ በዚሁ የምርጫ ስነ ስርዓት ላይ 38 እጩ ተወዳዳሪዎች ለጠቅላላው ጉባኤው ቀርበው ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የድጋፍና የተቃውሞ ድምጽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ጠቅላላ ጉባኤው ድምጽ ከሰጠባችው 38 እጩዎች መካከል ለሚቀጠሉት 2 ዓመታት የሚያገለግሉትን  25 የማዕከላዊ ምክር ቤት አባላትን በሚስጥር የድምጽ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት የመረጠ ሲሆን በመቀጠልም 3 የኦዲትና ኢኒስፔክሽን ኮሚቴ አባላትን መርጧል፡፡
በዚህም መሰረት የተመረጡት የማዕከላዊ ምክር ቤትና የኦዲትና ኢኒስፔክሽን ኮሚቴ አባላት የሚከተሉት ናቸው፡፡
1.    አቶ ሙሼ ሰሙ
2.    አቶ ልደቱ አያሌው
3.    ወ/ሮ ሶፍያ ይልማ
4.    አቶ መስፍን መንግሰቱ
5.    አቶ ነጻነት ደመላሽ
6.    አቶ አዳነ ታደሰ
7.    አቶ ቴዎድሮስ ውድነህ
8.    አቶ አንዳርጋቸው አንዱአለም
9.    አቶ ጌታሁን ብሬ
10.    አቶ ጫኔ ከበደ
11.    ዶ/ር ባንትይገኝ ታምራት
12.    አቶ ሄኖክ ሄደቶ
13.    አቶ ጌትዬ አስፋው
14.    ወ/ሪት ሳባ ተሾመ
15.    አቶ እያሱ መኮንን
16.    አቶ ተስፋ መስፍን
17.    አቶ ኤርሚያስ ባልከው
18.    አቶ ጐሹ አውድው
19.    አቶ አለማየሁ ባልዳ
20.    አቶ ደረጀ ደበበ
21.    ወ/ሪት ሳራ ይሳቅ
22.    አቶ ሰለሞን ሰንደቁ
23.    አቶ ወንዶሰን ተሾመ
24.    ወ/ሪት ጽጌ ጥበቡ
25.    አቶ ሳህሉ ባየ

የኦዲትና ኢኒስፔክሽን ኮሚቴ አባላት
1.    አቶ ግዛቸው አንማው
2.    አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ
3.    አቶ አስማማው ተሰማ

በሚቀጥለው ቀን የተሰየመው የማዕከላዊ ምክር ቤት  የፓርቲውን  ከፍተኛ አመራር አባላትና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የመረጠ ሲሆን፤ በመቀጠልም የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን የዘርፍ ድልድል አድርጓል፡፡
በዚህም መሰረት የተመረጡት የስራ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባለት
1.    አቶ ሙሼ ሰሙ የፓርቲው ፕሬዚዳንት
2.    ወ/ሮ ሶፍያ ይልም የፓርቲው ም/ፕሬዚዳንት
3.    አቶ መስፍን መንግስቱ የፓርቲው ዋና ጸሐፊ  በመሆን ለሚቀጥሉት 2 ዓመታት እንዲያገለግሉ ተመርተዋል፡፡

በስራ አስፈጻሚነት ፓርቲውን ለሚቀጥሉት 2 ዓመታት እንዲያገለግሉ የተመረጡት አበላት
1.    አቶ ነጻነት ደመላሽ የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ
2.    ወ/ሮ ሳራ ይስሀቅ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3.    አቶ ሳህሌ ባየ የፓርቲው የውጭ ግንኙነት ኃላፊ
4.    ዶ/ር ባንትይገኝ ታምራት የፓርቲው  የጥናትና ምርምር ኃላፊ
5.    አቶ ጫኔ ከበደ የፓርቲው የፋይናንስ ኃላፊ
6.    አቶ ወንዶሰን ተሾመ የፓርቲው የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ናቸው፡፡

ይህ 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመተዳደርያ ደንቡ መሰረት ለሁለተኛ ጊዜ የፓርቲውን ፕሬዚዳንት ያሰናበተ ሲሆን የፓርቲውን ፕሬዚዳንት የአገልግሉት ዘመን በመተዳዳርያ ደንቡ በመገድብ ረገድ ብቸኛ የሆነው ኢዴፓ የፓርቲውን ፕሬዚዳንት በተቀመጠላቸው የስልጣን ዘመን እንዲለቁ ማድረጉ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ታሪክ ፈር ቀዳጅነቱን አስመስክሯል፡፡

የኢዴፓ 5ኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ተወያይቶ አቋም የወሰደባቸው አገራዊ አጀዳዎች (pdf)

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter