የኢዴፓ ፕሬዚዳንት ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ጋር ትውውቅ አደረጉ

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)  ፕሬዚዳንት እና የቀድሞው ፕሬዚዳንት መጋቢት 12 ቀን 2003 ዓመተ ምህረት በእስፓኝ ኢምባሲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተከበሩ የዩናይትድ ሰቴትስ ኦፍ አሜሪካ አምባሳደር፣ የተከበሩ ከአውሮፓ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ  የተውጣጡ እንዲሁም የተከበሩ የጃፓን እና የሜክሲኮ  አምባሳደሮች በተገኙበት ተወያዩ፡፡

በስብሰባው  በጥቅሉ በፓርቲው ወቅታዊ እንቅስቃሴ፤ በአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታና በወቅታዊ ዓለምአቀፍ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርጓል፡፡ በዚህ ውይይት ላይ ከአዲሱ የኢዴፓ ፕሬዚዳንት ከአቶ ሙሼ ሰሙ ጋር ትውውቅ የተደረገ ሲሆን የተከበሩት አምባሳደሮችም ለተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ለአቶ ልደቱ አያሌው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ስብሰባው ትኩረት ሰጥቶ ከተወያየባቸው ጉዳዮች መካከል የኢዴፓ የወደፊቱ እንቅስቃሴና ራዕይ፣ ምርጫ 2002ና ውጤቱ፣ የምርጫው ውጤት በፓለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ላይ የሚኖረው እንደምታና በአጠቃላይ የፖለቲካ ምህዳሩ ላይ የተደቀኑ መሰናክሎችን በመፍታት ዙርያ ከዓለም እቀፍ ማህበረስቡ የሚጠበቀውን ድጋፍ አስመልክቶ የተነሱት ነጥቦች በተለይ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
አንድ ሰዓት የፈጀው ወይይቱ ተመሳይ ውይይቶችን እንደአስፈላጊነቱ በማድረግ ጠቀሜታ ላይ መግብባት ፈጥሮ ተጠናቋል፡፡

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter