በመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዙሪያ ያለውን ስር የሰደደ ችግር፤ ለችግሩ ምክንያት በሆነ አስተሳሰብና አሰራር መፍታት አይቻልም

በቅርቡ ዜጎች የከተማ ቦታን በሊዝ ብቻ እንዲይዙ የሚያስገድድ አዲስ አዋጅ  ታውጇል፡፡ ይህ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  የታወጀ አዋጅ “ለተሳለጠ፣ ለውጤታማ ለፍትሐዊና ለጤናማ የመሬትና የመሬት ነክ ንብረት ገበያ ልማት፣ ቀጣይነት ለተላበሰ የነጻ ገበያ ሥርዓት መስፋፋት፣ ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲኖር ለማድረግ ”  እንደታወጀ  በዚሁ በአዋጁ ላይ ተጠቅሷል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ስለአዋጁ አስፈላጊነት የተሰጠው ምክንያትና የአዋጁ ይዘት ሲታዩ ለየቅል ናቸው፡፡ በአዋጁ መሰረት ዜጎች በከተማ ቦታ ላይ ያላቸው የባለይዞታነት መብት በሊዝ ስምምነትና ኪራይ መሠረት ብቻ ይሆናል፡፡ አዋጁ ማንኛውም ግለሰብ በግዢም ሆነ በተለያየ መንገድ ለዘመናት ንብረቱ ሆኖ የቆየውን የመሬት ባለቤትነት መብት ወደ መንግስት አዛውሯል፡፡  ማንኛውም ዜጋ በስሙ  በተመዘገበለት የከተማ ቦታ ላይ ባፈራው ቋሚ  ሀብትና ይህንኑ ሀብት ለማፍራት ምክንያት በሆነው መሬት መካከል ምናባዊ ልዩነት በመፍጠር ዜጎች የተረጋገጠላቸው መብት  ይዞታው  ላይ ላፈሩት ንብረት ብቻ እንዲሆን  ይደነግጋል፡፡ ከሊዝ አሰራሩ ውጭ ቀደም ብለዉ የተያዙ ቦታዎች ላይ የባለይዞታነት ዝውውር በተደረገ ቁጥር ከውርስ ውጪ ቦታው የተላለፈለት ሰው ባለይዞታነት የሚረጋገጠው ወይም ባለይዞታው ንብረቱን ማዘዋወር የሚችለው በሊዝ ሥሪት ብቻ እንዲሆን ደንግጓል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ (pdf)

 

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter