Blog

የኢትዮጵያን ህዝብ ድሀ አድርጎ የመግዛት ሥትራቴጂ

በጫኔ ከበደ ከኢ.ዴ.ፓ ፕሬዘዳንት (በግል) ኢትዮጵያ የግዛት መሬቷን በዲፕሎማሲያዊ ሂደትም ሆነ በጦርነት ማስከበር ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ የእስተዳደር /የአገዛዝ/ ሥርዓቶችን አስተናግዳለች የመንግስት ቅርፅነትን ይዛ መኖር ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ ከታሪክ እንደምንረዳው የብዙ ሺህ ዓመቶችን ዕድሜ አስቆጥራለች በትንሹ የ3ሺ ዓመት ዕድሜ፡፡ በዚህ ረጅም የመንግስትነት ቅርፅና አስተዳደር በርካታ ነገስታትን አሰተናግዳለች መንግስታት የየራሳቸው አሰራርና አገዛዝ ቢኖራቸውም ትውልድ ግን ከዘር […]

ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርላማ አባልና መፅሀፋቸው

ኤርሜያስ ባልከው  የኢዴፓ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ PDF በአገራችን ከተካሄዱት ምርጫዎች መካከል ምርጫ 1997 ዓ.ም የተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ልዩ ታሪካዊ ምርጫ ነበረ ማለት ይቻላል፡፡  በዚህ ታሪካዊ ምርጫ ከሚነሱ የምርጫ ሀይሎች አንዱ ደግሞ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ የተባለው የአራት ፓርቲዎች ስብስብ ነው፡፡ ይህ ምርጫ ብዙ አስተማሪ አሳዛኝ ክስተቶችን ያስተናገደ ምርጫ እንደመሆኑ በዚህ ዙሪያ የተለያዩ መጽሀፎችና ፁሁፎች ተፅፈዋል፡፡ […]

ሦስተኛው መንገድ

በኤርሚያስ ባልከው (የኢ.ዴ.ፓ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ) PDF ለዚህ ፅሁፍ ምክንያት የሆነኝ ማክሰኞ ታህሳስ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ቅፅ 02 ቁጥር 50 ኢትዮ- ምህድር ጋዜጣ ላይ የኢዴፓ “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” በሚል ርዕስ አቶ ጌታነህ አስቻለው የተባሉ ፀሐፊ የፃፉትን ፅሁፍ ካነበብኩ በኋላ ነው፡፡ በኔ በኩል የፅሁፍ መፃፍ ሀሳቡን የበለጠ ለማብራራት እድል የሚሰጥ በመሆኑ ደስተኛ ነኝ፡፡ ነገር ግን ፀሀፊው […]

ስደተኞችን እንደ መንግስት “የገቢ ርዕስ” ከማየት አባዜ ባሻገር

ከሙሼ ሰሙ በመጀመርያዎቹ ሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶችን አስመልክቶ ባረቀቀው ደንብ አንቀጽ 18 ላይ ስደተኞችን ወይም መጤዎችን ስለማፈናቀል ድንጋጌ አውጥቶ ነበር፡፡ ድንጋጌው እንደሚያትተው ከሆነ መጠነ ሰፊ በሆነ ደረጃ፣ ያለማመዛዘን፣ ልዩነት ሳያደርግ ሃይል በታከለበት ሁኔታ መጤዎችንና ስደተኞችን ማፈናቀል በሰብአዊ ፍጡር ላይ እንደተሰራ ከባድ ወንጀል ተቆጥሮ አባል ሃገራት በድርጊቱ ፈጻሚ መንግስታት […]

አቶ ልደቱ ወደ ፖለቲካ ተመለሱ (አዲስ አድማስ)

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቢሆንም ግን ፈተናውን ወድቋል የሚሉት አቶ ልደቱ አያሌው፤ የኢኮኖሚ እድገቱን መካድ ስህተት ነው፤ እድገቱ ዘላቂነት እንደሌለው አለመገንዘብም ስህተት ነው በማለት የኢዴፓ “ሦስተኛ አማራጭ” የተሰኘ የኢዴፓ አቋምን ይተነትናሉ፡፡ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች መዳከም አንዱ ምክንያት የመንግስት ተጽእኖ እንደሆነ አቶ ልደቱ ገልፀው፤ ነገር ግን ህዝቡን አሰባስቦ በመታገል የመንግስትን ተጽእኖ ማስቆምና ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡ ይልቅስ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ራሳቸውን […]

እውነትም “ያለበት” ይገንበት እንዳይሆን ?

ከሙሼ ሰሙ(የኢዴፓ ፕሬዚዳንት) “በዓለም ላይ ያሉ  ሃገሮች የራሳቸው መከላከያ ሰራዊት አላቸው፡፡ የኛ መከላከያ ሰራዊት ግን አልጄሪያ የሚባል የራሱ ሃገር አለው፡፡”                                                                         የአልጄሪያ ሕዝብ አዲስ አድማስ ጋዜጣ በዜና ዘገባው ላይ የመከላከያ ሳምንትን አስመልክቶ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቋማችንን እንድንገልጽ እድል ሰጥቶን ነበር፡፡ በዚህ እድል ሃሳባቸውን ከገለጹት ተጋባዦች መካከል አንዱ እኔ ነኝ፡፡ ዜና ዘጋቢው ለአምዱ ስፋት ይመጥናል ባሉት ልክ […]

“ገቢዎች ከመንግስትም በላይ ስልጣን የተሰጠው አካል ነው” አቶ ሙሼ ሠሙ – የኢዴፓ ሊቀመንበር

ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሰሞኑን በሙስና በጠረጠራቸው ትላልቅ ባለስልጣናትና ባለሃብቶች ላይ የወሠደውን እርምጃ እንዴት ይመለከቱታል? ለኛ ይሄ ነገር የተለየ እውቀት የሚጠይቅ አይደለም፡፡ ስቴት ካፒታሊዝም ወይም መንግስታዊ ከበርቴ የምትለው ስርአት አይነተኛ መገለጫው ነው፡፡ ነጋዴውን ህብረተሠብ የሚያሸማቅቅ፣ የመንግስትን ሚና የሚያጐለብት ነው፡፡ የንግዱን ማህበረሠብ የመንግስት ባለስልጣን ጥገኛም እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ጉዳዩን ለማስፈፀም፣ ስራውንም ለመስራት ሣይወድ በግዱ የመንግስት ባለስልጣናት አሽከር ይሆናል፡፡ […]