ኢዴፓ የምርጫ መወዳደሪያ ማኒፌስቶውን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)‹‹ኢዴፓ የዛሬውና የነገው ትውልድ ፓርቲ›› በሚል መፈክር ያዘጋጀው የ2007 ዓ.ም. የምርጫ መወዳደሪያ ማኒፌስቶውን የካቲት 18 ቀን 2007 ዓ.ም. ይፋ አደረገ፡፡

በወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል ላይ ልዩ ትኩረት አድርጓል፡፡ ፓርቲው በማኒፌስቶው ላይ እንዳስታወቀው፣ በመጪው ግንቦት በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ የሕዝብን ይሁንታ አግኝቶ ከተመረጠ በአገሪቱ ዘላቂ የፖለቲካ መረጋጋት ለመፍጠር፣ ቀጣይነት ያለውና በየደረጃው የሚገኘውን የኅብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣትና ማኅበራዊ ደኅንነትን በአገሪቱ ለማስፈን የሚያስችሉትን የተለያዩ አማራጮችን ይዞ መቅረቡን ገልጿል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ (ሪፖርተር)

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter