የአገራችን የፖለቲካ ቀውስ መንስዔና መፍትሄ፣ በምክኒያታዊ አይን

Lidetu Ayalew1.መግቢያ
በአሁን ወቅት በአገራችን የተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ ለብዙዎች ድንገተኛና አስደንጋጭ ሆኗል፡፡ በእርግጥ ለአንዳንዶቻችን ክስተቱ አሳዛኝ ቢሆንም ድንገተኛና አስደንጋጭ ግን አልሆነም፡፡ እኔም ሆንኩ አባል የሆንኩበት ኢዴፓ በአንድ በኩል በተገቢው ወቅትና ሁኔታ እራሱን ማደስ ወይም መለወጥ የማይችል ማንኛውም መንግስት የመጨረሻ እጣ-ፋንታው በዚህ አይነት አስቀያሚ ሁኔታ ማለትም በአብዮትና በጠመንጃ ከስልጣን መውረድ መሆኑን ስለምንገነዘብ፤ በሌላ በኩል እንዲህ ዓይነቱ አስቀያሚ የለወጥ ሂደት በአገራችን እንዳይከሰት በማሰብ የፅንፈኝነት ፖለቲካ ተወግዶ ምክንያታዊ የፖለቲካ ባህል በአገራችን እንዲፈጠር ለብዙ አመታት ያለ አድማጭ ስንጮህ ስለኖርን ለእኛ የወቅቱ ክስተት የሚጠበቅ አሳዛኝ ክስተት እንጂ ድንገተኛና አስደንጋጭ አልሆነም፡፡

የሆነ ሆኖ በአገራችን ለውጥ እንዲመጣ፣ የሚመጣው ለውጥ ግን የአገርን ህልውና ጥያቄ ውስጥ የማያስገባና እንዳለፉት የአገራችን የመንግስት ለውጦች አንድን ገዥ በሌላ ገዥ የሚተካ ሳይሆን እውነተኛ የስርዓትና የአስተሣሰብ ለውጥ እንዲሆን ለምንፈልግ ኃይሎች የወቅቱ ክስተት አስቸጋሪ አጣብቂኝ /dilemma/ ውስጥ የከተተን መሆኑን መካድ አይቻልም፡፡ አጣብቂኝ ውስጥ የገባነው ያለምክንያት ሳይሆን በአንድ በኩል በስልጣን ላይ የሚገኘው መንግስት በእውነተኛ የህዝብ ምርጫ ስልጣኑን ለማጋራትም ሆነ ለመልቀቅ ፈቃደኛ የማይሆን አባገነናዊ መንግስት መሆኑን ከተግባራዊ ልምዳችን ጠንቅቀን ስለምናውቅ በሰላማዊ የህዝብ ትግል ተገዶ ለውጥን እንዲቀበል እንፈልጋለን፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በድርጅትና በመርህ ሳይሆን በስሜት፣ በምሬትና በጥላቻ እየተመራ ያለው ያልተቀናጀ የህዝብ ትግል መንግስትን ከስልጣን ከማውረድ አልፎ ጭራሹንም መንግስትና አገር አልባ ሊያደርገን ይችላል የሚል ከተጨባጭ ምክኒያት የመነጨ ስጋት ስላለን የወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታ አስቸጋሪ አጣብቂኝ ውስጥ አስገብቶናል፡፡

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ (pdf)

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter