ኢዴፓ የአገር አቀፍ ፓርቲ መስራች አባላቱን በሁሉም ክልሎች አስፈረመ

በአዲሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ መሰረት ነባር ፓርቲዎችም የመስራች አባሎቻቸውን ቁጥር በማሳደግ ዳግም እንዲመዘገቡ የሚያስገድድ መሆኑ ይታወቃል።

ምንም እንኳ ፓርቲያችን በከፍተኛ ውጣ ውረድ ውስጥ የቆየና አሁንም የተሟላ ድርጅታዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ጽ/ቤቶቹና ሰነዶቹ ያልተመለሱለት ቢሆንም እንደ ሀገርአቀፍ ፓርቲነቱ የሚጠበቅበትን የ 10ሺህ የመስራቾች ፊርማ ላለፉት ጥቂት ሳምንታት ሲያከናውን ቆይቷል።

በዚህም ሕጉ የሚጠይቀውን ስብጥር በጠበቀ መልኩ 15,600 (አስራ አምስት ሺህ ስድስት መቶ) ተጨማሪ የመስራች አባላትን ከሁሉም ክልሎች ማስፈረም ተችሏል።

ለዚህ ስኬት እንበቃ ዘንድ ጊዜአችሁን፣ ገንዘባችሁን፣ ጉልበታችሁን እና ዕውቀታችሁን ያበረከታችሁ የድርጅታችን ዓባላትና ደጋፊዎች ከፍተኛ ምስጋና ይገባችኋል።

በመላው ሀገራችንና ከሀገር ውጭ የምትገኙ የኢዴፓ ቤተሰቦች በሁለት ወራት ውስጥ ለምናደርገው ጠቅላላ ጉባዔ የተጠናከረ ዝግጅት እንድታደርጉ በዚህ አጋጣሚ እያስታወስን ለእስከአሁኑ ስኬት እንኳን ደስ ያለን ለማለት እንወዳለን።

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter