ኢዴፓ ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለታላቁ ህዳሴ ግድብ ወቅታዊ ሁኔታ በተደረገ ገለጻ ላይ በመገኘት የ 20ሺህ ብር ቦንድ ገዛ!

በገለፃው ላይ የተገኙት የኢዴፓ ፕሬዚደንት አቶ አዳነ ታደሰ በግድቡ ግንባታ ዙሪያ ፓርቲያቸው ዛሬም እንደተለመደው ያለውን ሙሉ ድጋፍ የገለጹ ሲሆን በተጨማሪም ፓርቲው ካለው ውስን አቅም ወጪ በማድረግ የ20ሺ ብር ቦንድ በመግዛት ድጋፉን በተግባርም ጭምር አሳይተዋል።

ኢዴፓ አባል የሆነበት አብሮነት ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት (አብሮነት) ለግድቡ ግንባታ ያለውን ቋሚ ድጋፍ በማጽናት በተለይ በሕዳሴው ግድብ ውሃ አሞላል ዙሪያ ከግብጽና ሱዳን ጋር የሚደረገው ድርድር በምንም መንገድ የውሃ ድርሻን የሚመለከት ሊሆን እንደማይገባና የአሞላል ድርድሩም ቢሆን በአፍሪካ ማዕቀፍ ብቻ ሊከወን እንደሚገባ በተደጋጋሚ ሲያሳስብ መቆየቱ ይታወቃል።

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter