የኢዴፓ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ አደረገ

የኢዴፓ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በ18/1/13 አስቸኳይ ስብሰባ አደረገ። ስራ አስፈፃሚው በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይና በፓርቲው ወቅታዊ እና ቀጣይ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ተነጋግሮ አቅጣጫ አስቀምጧል። ወቅታዊ የአገሪቷን ሁኔታ በተመለከተ ከእለት ወደ እለት የአገሪቷ ሁለንተናዊ ችግር እየተባባሰ መምጣቱን የገመገመ ሲሆን፣ ይሄ የአገሪቱ ውስብስብ ችግር በተባባሰበት ሁኔታ ወደ ምርጫ ለመግባት መወሰኑ የበለጠ ወደ ባሰ ቀውስ ውስጥ የሚከት መሆኑ ታምኖበታል። ስለዚህ አገራችንን ከዚህ ቀውስ ለመታደግ ሁሉን አቀፍ የእርቅና የሽግግር መንግስት መመስረት አለበት።

ለዚህ እንዲረዳ ሁሉን አቀፍ የውይይት መድረክ እንዲመቻች ፖርቲያችን ግፊት ማድረጉን እንዲቀጥል አቅጣጫ አስቀምጧል። የፖርቲውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በቀጣይ 2013 አ/ ም የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራትን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ዝርዝር የስራ እቅድ በሚቀጥሉት ሳምንት ፅ/ቤት ገቢ እንዲያደርጉ እና እቅዱ ተገምግሞ በአስቸኳይ ወደ ስራ እንዲገባ ተወስኗል። ለዚህም አባላት እና ደጋፊዎች በገንዘብ፣ በሞራል እና በሃሳብ ከጎናችን በመሆን ትግላችንን እንዲደግፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter