ከኢ.ዴ.ፓ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ( አብን) ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ/ም በአማራ ክልል በተለያዪ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል። ነገር ግን የክልሉ መንግስት ሰልፉን መከልከሉን መረጃዎች እየጠቆሙ ነው። አንድ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ህገ መንግስታዊ መብት አለው። የክልሉ መንግስት የዜጎችን ተቃውሞ የማሰማት መብት በገሃድ ሲከለክል ማየት ስርዓቱ ምን ያህል አምባገነን እየሆነ እንዳለ የሚያሳይ ነው። ስለዚህ የክልሉ መንግስት በፓርቲው ላይ የጣለውን የመብት ክልከላ በአስቸኳይ እንዲያነሳ እንጠይቃለን። ዜጎች እንዳይቃወሙ እና በወገኖቻቸው ማንነት ላይ ያነጣጠረውን ግድያ፣ ጭቆና፣ ስቃይ እና ብሶት እንዳያሰሙ መከልከል ካለፈው ስርዓት አለመሻል መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

የኢዴፓ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter