ኢዴፓ፤ ኢሀንና ኅብር ኢትዮጵያ በጋራ ማኒፌስቶ ለመወዳደር የመጀመርያውን ስምምነት ፈጸሙ

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሀን) እና ኅብር ኢትዮጵያ ‹‹የኢትዮጵያ ኮንፌዴራሊስት ኃይሎች በሀገሪቱ ኅልውና ላይ ሊፈጥሩት የሚችሉትን አደጋ ለመቋቋም አልመናል›› በሚል ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት ፈጠሩ::  

ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠትን በሚመለከት

የአገራችን የህልውና አደጋ በእጅጉ ያሳሰበንና አገራችንን ከዚህ የህልውና አደጋ መታደግ የአገሪቱ የፖለቲካ ሃይሎች ቀዳሚ ወቅታዊ ትኩረት መሆን ይገባዋል ብለን ያመን ሶስት አገር አቀፍ ፓርቲዎች ህብር ኢትዮጵያ፣ ኢዴፓ እና ኢሀን የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም በጋራ እና በትብብር ለመስራት ወስነናል። በስምነታችን ዙሪያ በአዜማን ሆቴል ማክሰኞ በ21/4/2012 ዓ.ም በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ እንሰጣለን ሁላችሁም የመገናኛ ብዙሃን ተጋብዛችኋል።

ከኢዴፓ ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

ቀዳሚ ትኩረት ለአገራዊ ህልውና!! ኢዴፓ በሃያ ዓመታት የትግል ጉዞው ለሶስተኛ ጊዜ የገጠመውን የህልውና አደጋ እልህ አስጨራሽ የሆነ ትግል በማካሄድ አክሽፎታል፡፡ በገዥው ፓርቲ፣ በኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ፣ በግንቦት 7 እና በአራት የራሳችን የፓርቲ አባላት ትብብርና ቅንጅት የፓርቲያችንን ህልውና ለማጥፋት ላለፉት ሶስት ዓመታት የተካሄደብንን ዘመቻ በማያዳግም ሁኔታ አክሽፈን ወደ ትግሉ ጎራ እነሆ ተቀላቅለናል፡፡ የኢዴፓ አመራር አባላት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ […]

Ethiopian Democratic Party

የኢዴፓ ኦዲትና ኢንስፔክሽን አባላት በኢዴፓ ብሄራዊ ምክር ቤት ላይ የተጣለው እገዳ እንዲነሳ ጠይቁ

የኢዴፓ ኦዲትና ኢንስፔክሽን 3 አባላት በጋራ ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ አስገቡ፡፡ በደብዳቤያቸው በኢዴፓ ብሄራዊ ምክር ቤት ላይ የተጣለው እገዳ እንዲነሳ ጠይቀዋል፡፡ ሙሉ ደብዳቤያቸውን ከዚህ በታች አቅርቤዋለው፡፡ ቀን- 19/09/2011 ዓ.ም ቀን- 19/09/2011 ዓ.ም ለክብርት ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አዲስ አበባ ጉዳዩ፤- ላለፉት አንድ ዓመታት የኢዴፓ ብሔራዊ ምክር ቤት ላይ ተጥሎ የቆየው እገዳ እንዲነሳ […]

Ethiopian Democratic Party

ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ

ቀን- 02/09/2011 ለክብርት ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳየኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢአዲስ አበባ ጉዳዩ፡- አቤቱታን ማቅረብን ይመለከታልቀደም ሲል በስራ ላይ የነበረው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህግ ከተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት ውጭ በኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የብሔራዊ ምክር ቤት የስራ እንቅስቃሴ ላይ እገዳ መጣሉ ይታወቃል፡፡ በዚህም ምክንያት የፓርቲው ከፍተኛ የስልጣን አካል የሆነው የኢዴፓ ብሔራዊ ምክር ቤት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና […]

የወቅቱን የኢህአዴግ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ግምገማ አስመልክቶ ከኢዴፓ የተሰጠ መግለጫ!

በቅርቡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ አድርጎ ያካሄደውን ግምገማ አስመልክቶ በግንባሩ መሪዎች እየተሰጡ ያሉ መግለጫዎችን ኢዴፓ በትኩረት እየተከታተላቸው ይገኛል፡፡ የኢዴፓ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ይህ የወቅቱ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ግምገማ፤- ምን ያህል ካለፉት ጊዜያቶች ግምገማ የተለየ እንደሆነ፣ በአሁኑ ወቅት በአገራችን ለተከሰተው ከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት የሆኑ ችግሮቻችን ምን ያህል በጥልቀት ተዳሰዋል፣ የታሰበው […]

ሃቀኛ ትኩረት ለውጤታማ ድርድር ወሳኝ ነው!

በሃገራችን ለተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት በማሰብ በሃገሪቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የቅድመ ድርድር ውይይት ከተጀመረ ከሁለት ወር በላይ ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡ በዚህ ግዜ ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች በድርድሩ የአካሄድ ስነ-ስርዓት ዙሪያ ለ7 ግዜ ተገናኝተን የተወያየን ቢሆንም በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ያለው ግንኙነት ወደ ተሻለ የመግባባትና የመቻቻል መንፈስ ከመሸጋገር ይልቅ እንደተለመደው ገና ከጅምሩ የመክሸፍ አደጋ እየታየበት ነው፡፡ በቅድሚያ […]