Blog

የኢዴፓ የሥራ አስፈፃሚ የክልል ቢሮዎች ጉብኝት

የኢዴፓ የሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ወንድወሰን ተሾመና አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ከታህሳስ 25 ቀን  2006 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2006 ዓ.ም ለስድስት ቀናት የቆየ የሥራ ጉብኝት በደሴና በላሊበላ አካሄዱ፡፡ በዚህም ጉብኝት በመጀመሪያ በደሴ አራዳ ገበያ አካባቢ ያለውን ቢሮ የተመለከቱና ቢሮውንም እንዳዲስ ያጠናከረ ሲሆኑ በመቀጠልም በላሊበላ ከተማ ቀደምት በሚባለው ቦታ አካባቢ የሚገኘውን ቢሮ ከተመለከቱና በዛው የሚገኙ […]

ኢዴፓ አዲስ ፕሬዚዳንት መረጠ

የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ማዕከላዊ ምክር ቤት ባለፈው እሑድ ፓርቲውን ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚመሩትን ፕሬዚዳንት መረጠ፡፡ ፓርቲውን በፕሬዚዳንትነት የሚመሩት አቶ ጫኔ ከበደ ናቸው፡፡ከአቶ ጫኔ በተጨማሪ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ዋና ጸሐፊና ዘጠኝ ሥራ አስፈጻሚዎችን መርጧል፡፡ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ባንተይገኝ ታምራት ሲሆኑ፣ ዋና ጸሐፊ ሆነው የተመረጡት አቶ ሳህሉ ባዬ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል ፓርቲውን በፕሬዚዳንትነት […]

ኢዴፓ በቸሃ ወረዳ እምድብር ከተማ አስራ ሶስተኛ ቢሮውን ከፈተ

የኢትዮጵያውን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኢዴፓ) በቸሃ ወረዳ እምድብር ከተማ  አስራ ሶስተኛ ቢሮውን ቅዳሜ ሕዳር 8 ቀን 2005 ዓ.ም ከፈተ፡፡ የቸሃ ወረዳ የኢዴፓ ደጋፊዎች በተለያየ ጊዜ የፓርቲውን ዓላማዎች፣ አቋሞችና አሰራሮች ላይ ሰፊ ውይይት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን ይህ ውይይታቸው ፍሬያማ  ውጤት ሊያስመዘግብ በመቻሉ፤ የአካባቢው የኢዴፓ ደጋፊ ነዋሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ቢሮ በመክፈት በኢዴፓ እውቅና እንዲሰጣቸው ጥያቄ በማቅረባቸውና ፓርቲው ጥያቄያቸውን በከፍተኛ […]

በመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዙሪያ ያለውን ስር የሰደደ ችግር፤ ለችግሩ ምክንያት በሆነ አስተሳሰብና አሰራር መፍታት አይቻልም

በቅርቡ ዜጎች የከተማ ቦታን በሊዝ ብቻ እንዲይዙ የሚያስገድድ አዲስ አዋጅ  ታውጇል፡፡ ይህ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  የታወጀ አዋጅ “ለተሳለጠ፣ ለውጤታማ ለፍትሐዊና ለጤናማ የመሬትና የመሬት ነክ ንብረት ገበያ ልማት፣ ቀጣይነት ለተላበሰ የነጻ ገበያ ሥርዓት መስፋፋት፣ ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲኖር ለማድረግ ”  እንደታወጀ  በዚሁ በአዋጁ ላይ ተጠቅሷል፡፡

ቅድሚ ትኩረት የዜጎችን ህይወት ለማዳን ይሁን

ዛሬም እንደገና የአገራችን ስም በድርቅና በረሃብ ምክንያት የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን መነጋገርያ ርዕስ ሆኖል፡፡ በዝናብ እጥረት ምክንያት በሁሉም የምስራቅ አፍሪካ አገሮች የተከሰተው ድርቅና ረሃቡ  ዓለምን እያነጋገረ ቢሆንም  የድርቅ ውጤት የሆነውን ረሃብ አስቀድሞ ከመተንበይ ጀምሮ ዜጎችን ከሞትና ከስደት ከመከላከል አኳያ የኢህአዴግ መንግስት ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዳልተወጣ ከዓለም አቀፍ ሪፖርቶች መረዳት ይቻላል፡፡

ከአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ኢ. ቦዝ እና በአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ዴፕዩቲ አሲስታንት ከሆኑት ካርል ኢ. ዋይኮፍ ጋር በኢዴፓ ጽ/ቤት የተደረገ ውይይትና የስራ ጉብኝት ሪፖርት

የተከበሩ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ኢ.ቦዝ እና የተከበሩ በአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ዴፕዩቲ አሲስታንት  የሆኑት ካርል ኢ. ዋይኮፍ ከኢዴፓ ፕሬዚዳንት ከአቶ ሙሼ ሰሙ ጋር በኢዴፓ ጽህፈት ቤት በውቅታዊ ጉዳች ላይ  ውይይት አደረጉ፡፡ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት በላከልን ዜና መሰረት ቅደሜ ከሰዓት በኃላ በኢዴፓ ጽ/ቤት በተካሄደውና  አንድ ሰዓት ያህል በፈጀው በዚህ ውይይት ላይ ከአምባሳደሩና ከአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ […]

የፓርቲውን ድርጅታዊ ብቃትና አቅም ለማጠናከርና የአባላትን ቁጥር ለማሳደግ በኢዴፓ ፕሬዚዳንት የሚመራ ቡድን የክፍለ ሀገር ቢሮዎች ጉብኝት ሊያካሄድ ነው፡፡

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በ5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት እንዲያገለግል አዲስ የተመረጠው አመራር እንዲያከውናቸው ከተወሰኑት መሰረታዊ ተግባራት መካከል አንደኛው  የፓርቲውን ድርጅታዊ ብቃትና አቅም ማጠናከርና የአባላትን  ቁጥር ማሳደግ በወሳኝነት ይጠቀሳል፡፡