ሁለተኛው ዙር የኢዴፓ ሥራ አስፈፃሚ አባላት ስልጠና ተካሔደ

Default Gallery Type Template

This is the default gallery type template, located in:
/home/edpoijbm/public_html/wp-content/plugins/nextgen-gallery/products/photocrati_nextgen/modules/nextgen_gallery_display/templates/index.php.

If you're seeing this, it's because the gallery type you selected has not provided a template of it's own.

እሁድ የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ የኢዴፓ ሥራ አስፈፃሚ አባላት በቅሎ ቤት በሚገኘው የፓርቲው ቢሮ ሥልጠና ወስደዋል፡፡ ስልጠናው በተከታታይነት የሚሰጥ ሲሆን የሚሰጠውም በፓርቲው ውስጥ እና በኢትዮጵያ ፖለቲካ የበርካታ ዓመታት ልምድ ባላቸው የፓርቲው አባላት ነው፡፡

የሁለተኛውን ዙር ሥልጠና የሰጡት የፓርቲው የቀድሞ ፕሬዘዳንት የነበሩት አቶ ልደቱ አያሌው ሲሆኑ የስልጠናው ርዕስ በተለያዩ አገራዊ ርዕሶች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡
ሥልጠናው ለአንድ ሙሉ ቀን የተሰጠ ሲሆን የሥራ አስፈፃሚ አባላት በሥልጠናው ላይ እንደተደሰቱ ገልፀዋል፡፡ ይህ ሁለተኛው ዙር ሥልጠና የአንደኛው ዙር ሥልጠና ተከታይ ሲሆን አንደኛው ዙር ጥቅምት 24 ቀን 2006 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ በአንደኛው ዙር ሥልጠና ላይ ስለ ኢትዮጵያዊነት እና ስለ አንገብጋቢ አገራዊ አጀንዳዎች ላይ አተኩሮ የነበር ሲሆን ሁለተኛው ዙር ሥልጠና ደግሞ በተለይ ያተኮረው በለውጥ ተዋናዮች፣ በትግል ስልት እና በርዕዮተ-አለም አሰላለፍ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ሥልጠናው በ3ተኛ ዙር በመጪው ወር የሚቀጥል ሲሆን ሥልጠናውም በአቶ ልደቱ አያሌው የሚሰጥ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter