ግዙፍ መንግስት ጉርድ ዜጋ

ከደቂቀ ኢዴፓ

እንደ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ባሉ ሶሻሊስት ዘመም መንግሰታት ዘንድ የዜጎች ሉአላዊነት በራሱ ሙሉ ሆኖ በህገ-መንግሰት ውስጥ የመካተት እድል ቢያገኝም እንኳን የግለሰቦች ሁለንተናዊ  የመብት ጥያቄዎች የብዙ ነገሮች ተቀጥላ ናቸው፡፡ በደርግ ዘመን በሕገ-መንግሰት ደረጃ ውንግርግር ባለ መልኩም ቢሆን የግለሰብ መብት ቢሰፍርም ለህዝብ ጥቅም በሚል ድፍን መፈክርና በተለያዩ ደንቦችና መመሪያዎች ስም የግለሰቦችን መቀነት ከማስፈታት ጀምሮ ጥረው ግረው ያፈሩት ቋሚ ኃብት በጠራራ ጸሐይ መውረሱና  በግል አቋማቸው ምክንያት በነጭ ሽብርም ሆነ በቀይ ሽብር  ውስጥ መታቀፍ ባለመቻላቸው መሰደዳቸውና መገደላቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ለቡድን መብት ቆመናል በሚሉ ስርዓቶች ውስጥ ግለሰቦች ለብዙሃን ጥቅም በሚል መንገላታታቸው፤ ፈለጉም አልፈለጉም በርዕዮተዓለም  ካልታቀፉ መገለልና መገፋት እጣ ፈንታቸው ነው፡፡  ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ (pdf)

Share this...
Share on Facebook
Facebook
Tweet about this on Twitter
Twitter