Ethiopian-Democratic-Party

ኢዴፓ ለሚቀጥለው አገር አቀፍ ምርጫ ያለውን እንቅስቃሴ ለማጠናከር የሚያስችሉ መዋቅሮችን ፈጠረ

የኢዴፓ የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ በሚቀጥለው አመት ለሚደረገው አገር አቀፍ ምርጫ በአዲስ አበባ እና በሌሎች አካባቢዎች ያለውን እንቅስቃሴ ለማጠናከር  የሚያስችሉ መዋቅሮችን ፈጠረ፡፡ ስለሆነም ዘጠኝ አባላት ያሉት የአዲስ አበባ ጊዜያዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ኃላፊነት በመከፋፈል ሥራ ጀምሯል፡፡ ጊዜያዊ ኮሚቴው ባካሄዳቸው ሁለት ስብሰባዎች አመራሩን መርጧል፡፡ በዚህም መሰረት አቶ ግዛቸው አንመው ሰብሳቢ፣ አቶ መንገሻ ገ/ሚካኤል ም/ሰብሳቢ ፤ አቶ ለማ ጪማ ፀሐፊ፤ ወ/ሪት አለም ዘውዱ ድርጅት ጉዳይ እንዲሁም አቶ አስማማው ተሰማ የኮሚቴው ህዝብ ግንኙነት በመሆን ተመርጠዋል፡፡ በዛሬው እለትም ኮሚቴው ሶስተኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል፡፡ በተያያዘ ዜናም በቦንጋ፣ በሀዋሳ፣ በወላይታ፣ በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ወሎ እና በሀረርጌ የፓርቲ መዋቅሮች የየአካባቢያቸውን አመራር በመምረጥ የእውቅና … [Read More...]

chane_Kebede_2

የኢዴፓ ፕሬዚደንት አቶ ጫኔ ከበደ የዶክትሬት ዲግሪያቸዉን አገኙ

በያዝነው አመት መግቢያ ላይ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ በፕሬዚዳንትነት የተመረጡት  አቶ ጫኔ ከበደ አሜሪካን አገር ከሚገኘው አትላንቲክ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ በዴቬሎፕመንት ስተዲስ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በትላንትናው እለት አገኙ፡፡ ዶ/ር ጫኔ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በሒሳብ ትምህርት ከአስመራ ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ በሁዋላ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በስታቲስቲክስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡ የማስተርስ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በዴቬሎፕመንት ኢኮኖሚክስ እ.ኤ.አ. በ2009 ዓ.ም. አግኝተዋል፡፡ በስራ አለም ዶ/ር ጫኔ በሚሊተሪ አቪዬሽን ውስጥ በከፍተኛ ቴክኒሺያንነት ከዛም ወደ አብራሪነት በማደግ እስከ ከፍተኛ አብራሪነት ደርሰዋል፡፡ ከዚያም በተለያዩ ቦታዎች የማስተማር ስራ ሰርተዋል፡፡ … [Read More...]

edp_regular_meeting

የኢዴፓ ብሔራዊ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን አካሔደ

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ብሔራዊ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን መጋቢት  7 ቀን  2006 አካሄደ። የፓርቲው የምክር ቤት ስብሰባ በየአራት ወር የሚደረግ ሲሆን አዲሱ ምክር ቤት መስከረም 26 ቀን 2006  ጠቅላላ ጉባኤው ከተሰየመ በኋላ ይህ ሁለተኛው መደበኛ ስበሰባ ነው። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ … [Read More...]

በሐረር ከተማ የተፈጠረው ችግር አስቸኳይ መፍትሄ ያሻዋል!

ቀን 02/07/2006 ዓ.ም ቁጥር ኢ.ዴ.ፓ.023/06 የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም ምሽት ሁለት ሰዓት አካባቢ በሐረር ከተማ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ተከስቷል፡፡ ከዚህ በፊትም በዚሁ አካባቢ ተደጋጋሚ የእሳት ቃጠሎዎች መከሰታቸው ይታወሳል፡፡ ችግሩ እንደተከሰተ መንግሥት ድርጊቱን የፈፀመውን አካል ለማወቅ የማጣራትና ህብረተሰቡን የማረጋጋት ሥራ መሥራት ሲገባው በተመሳሳይ ቀን በተቻኮለ ሁኔታ ግሬደር አቅርቦ አካባቢውን ማፅዳት በመጀመሩ ህብረተሰቡ በመንግሥት ላይ የተለያዩ ጥርጣሬዎች እንዲያድሩበት ምክንያት ሆኗል፡፡ በዚህም ምክንያት አላስፈላጊ ግጭት ተፈጥሮ ንብረት ወድሟል፣ የንግድ እንቅስቃሴ ተቋርጧል፣ በሰዎችና በሰላማዊ ህይዎታቸው ላይ መጠኑ ያልተረጋገጠ ጉዳት ደርሷል፡፡ ስለሆነም መንግሥት እንደነዚህ እና መሰል ችግሮች ሲከሰቱ በሰከነ መንገድና ግልፅነት ባለው አሰራር … [Read More...]

Ethiopian-Democratic-Party-Training-Workshop

ሁለተኛው ዙር የኢዴፓ ሥራ አስፈፃሚ አባላት ስልጠና ተካሔደ

እሁድ የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ የኢዴፓ ሥራ አስፈፃሚ አባላት በቅሎ ቤት በሚገኘው የፓርቲው ቢሮ ሥልጠና ወስደዋል፡፡ ስልጠናው በተከታታይነት የሚሰጥ ሲሆን የሚሰጠውም በፓርቲው ውስጥ እና በኢትዮጵያ ፖለቲካ የበርካታ ዓመታት ልምድ ባላቸው የፓርቲው አባላት ነው፡፡ የሁለተኛውን ዙር ሥልጠና የሰጡት የፓርቲው የቀድሞ ፕሬዘዳንት የነበሩት አቶ ልደቱ አያሌው ሲሆኑ የስልጠናው ርዕስ በተለያዩ አገራዊ ርዕሶች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ሥልጠናው ለአንድ ሙሉ ቀን የተሰጠ ሲሆን የሥራ አስፈፃሚ አባላት በሥልጠናው ላይ እንደተደሰቱ ገልፀዋል፡፡ ይህ ሁለተኛው ዙር ሥልጠና የአንደኛው ዙር ሥልጠና ተከታይ ሲሆን አንደኛው ዙር ጥቅምት 24 ቀን 2006 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ በአንደኛው ዙር ሥልጠና ላይ ስለ ኢትዮጵያዊነት እና ስለ አንገብጋቢ አገራዊ አጀንዳዎች ላይ አተኩሮ … [Read More...]

More Posts from this Category